8926 ነጻ የስልክ ጥሪ ማዕከል ስራ ጀመረ

8926 ነጻ የስልክ ጥሪ ማዕከል ስራ ጀመረ

============//============

የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ለተገልጋዮች የሚሰጠዉን አገልግሎት ለተገልጋዮቹ መረጃ ለመስጠት 8926 ነጻ የስልክ መስመር ስራ አስጀመረ።

 

ይህ ነጻ የስልክ መስመር ተገልጋዮች በየትኛውም የአገሪቱ አካባቢ ሆነው ጥያቄ፣ አስተያየት እና ጥቆማ እንዲያቀርቡበት እና ምላሽ እንዲያገኙበት በማድረግ መረጃዎችን በይበልጥ ተደራሽ የማድረግ ዓላማ ያለው ነው።

 

በመሆኑም የአስተዳደሩ ተግልጋዮች የጡረታ ነክ ጉዳዮችን በአካል መምጣት ሳያስፈልጋቸው በዚህ የስልክ መስመር በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

 

//****

ታህሳስ 17/2017

አዲስ አበባ

Share this Post