49ኛው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በደማቅ ሁኔታ ተከበረ

49ኛው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በደማቅ ሁኔታ ተከበረ 
=============//==========
የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳዳር በሃገር አቀፍ ደረጃ ለ49ኛ ጊዜ "ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል’’ በሚል መሪ ሃሳብ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን /ማርች 8/ በዓል የካቲት 28/2017 ዓ.ም የተለያየ ሁኔቶችን በማከናወን በደማቅ ሁኔታ አከበሩ፡፡
የበዓሉ መክፈቻ ንግግር ያደረጉ የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጥላሁን በቀለ እንዳሉት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1908 በኒውዮርክ ግዛት ከስራ ሰዓት እና ከክፍያ መሻሻል እንዲሁም ከምርጫ አሳታፊነት ጋር በተያያዘ ይታይ የነበረው ኢ- ፍትሃዊነት እንዲቀረፍ ለመጠየቅ ሴቶች ተቃውሞ በማስነሳታቸው ምክንያት የሴቶች ቀን አከባበር የተጀመረ መሆኑን ታሪክ የሚናገር መሆኑን ጠቅሰው ዛሬ የምናከብረው በዓልም ሴቶች በማህበረሰቡ የሚደርስባቸውን ጭቆና ተቋቁመው በፖለቲካው እና በምጣኔ ሃብቱ ያስመዘገቡት ውጤት የሚዘከርበት እና የሴቶችን ዕኩልነት ለማረጋገጥ የተለያዩ ስራዎች የሚሰሩበት ነው ብለዋል፡፡
ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚው እንዳሉት የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደርም የተቋቋመበትን ተልዕኮ ለማሳካት የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ በማሳደግ ረገድ በርካታ ስራዎችን በማከናወን ላይ የሚገኝ መሆኑን እና በተቋሙ የተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ሴቶች በአመራርነት እንዲመደቡ በማድረግ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ጥረት የተደረገ ቢሆንም በሚፈለገው ልክ በቂ ባለመሆኑ አስተዳደሩ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ 
የበዓሉን አከባበር አስመልክቶ የተዘጋጀ ሰነድ ለውይይት የቀረበ ሲሆን ሁላችንም በቤታችንም ሆነ በስራ ቦታችን በሁሉም መስክ የሴቶችን ተሳትፎ ማጠናከርና በሀገር ዕድገት ላይ ያበረከቱትን ጉልህ አስተዋጽኦ በማንሳት ማበረታታት እንደሚጠበቅ ተነስቷል። በሀገራችንም ሆነ በዓለማችን በሚታዩ ግጭቶች ላይ በዋናነት ሴቶች ለችግር ሲዳረጉ ታዝበናል፣ በመሆኑም የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ ለማሳደግ ሰላም ቅድሚያ የሚሰጠው ነውና ይህን ማረጋገጥ የሁላችንም ኃላፊነት መሆኑን ልንዘነጋ አይገባም ተብለዋል።
በበዓሉ አከባበር ላይ የአስተዳደሩ ከፍተኛ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች የተገኙ ሲሆን በሁሉም ሪጅን ጽ/ቤቶች የተለያዩ ሁኔቶችን በማከናወን እየተከበር እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡ 
//****
የካቲት 28/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ

Share this Post