2018 በጀት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ላይ ዉይይት ተደረገ

የ2018 በጀት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ላይ ዉይይት ተደረገ
=============//============
የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የ2018 በጀት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ከአጠቃላ የአስተዳደሩ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች ጋር ጥር 07 ቀን 2018 ዓ.ም ውይይት አደረጉ፡፡  

በውይይቱ የተገኙት የአስተዳደሩ ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ጥላሁን በቀለ እንዳሉት አስተዳደሩ በግማሽ ዓመቱ የዕቅዱን 97 በመቶ ማከናወኑን እና የተከናወኑ ስራዎች አፈጻጸማቸው የሚያበረታታ መሆኑን አንስተዋል፡፡ 

አክለውም አስተዳደሩ አሰራሩን በቴክኖሎጂ በማዘመን የአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍናን እና የፋይናንስ አስተማማኝነትን ለማረጋገጥ ኢላማ አስቀምጦ እየሰራ ያለ መሆኑን እና በዚሁም ለ118,952 የመንግሥት ሰራተኞች የማኅበራዊ ዋስትና መለያ ቁጥር በመስጠት የዕቅዱን 134 በመቶ ተከናውኗል ብለዋል። 

በሌላ በኩል የባህርዳር እና ሀዋሳ ህንጻዎች ተጠናቀው ለቢሮ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን እና ሌሎች በአዲስ አበባ እና በክልል ያሉ የህንጻ ግንባታ ፕሮጀክቶች በተቀመጠላቸው ጊዜ በማጠናቀቅ ለርክክብ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑም ተገልፀዋል፡፡

በውይይቱ ስኬታማ አፈጻጸሞች፣ በአፈጻጸም ሂደት ያጋጠሙ ተግዳሮቶች፣ የተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎች እና በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቷቸው የሚሰሩ  ተግባራት ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጓል፤ ጥያቄና አስተያየቶችም ተነስተው ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ 

://****
ጥር 08/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ

Share this Post