17ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በድምቀት ተከበረ

17ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በድምቀት ተከበረ

=========//=======

የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር አመራሮችና ሠራተኞች 17ኛውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ!”  በሚል መሪ ቃል ጥቅምት 4/2017 በድምቀት አከበሩ።

 

በበዓሉ አከባበር ላይ የአስተዳደሩ የኮርፖሬት ሪሶርስ ማኔጅመንት ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ምስጋና አድማሱ፣ ሠንደቅ ዓላማ የብሔራዊ አንድነት መገለጫ፤ ዜጎች አገራዊ ፍቅርና ብሔራዊ ስሜታቸውን የሚገልፁበት፤ ታሪካዊ ትስስርና ስነ-ልቦናዊ አንድነት የሚንፀባረቅበት የአንድነትና ህብረት ዓርማና ምልክት ነው ያሉ ሲሆን፣ ሀገራችን ክብሯን እና ነጻነቷን ጠብቃ፣ አሁን የተጋረጡባትን ፈተናዎች ሁሉ አልፋ፣ የብልጽግና ጉዞዋን ለማስቀጠል፣ ለበርካታ ሀገራትም የነጻነት ተምሳሌት የሆነውን የሠንደቅ ዓላማችንን ክብር በማስጠበቅ ለብሔራዊ አንድነታችንና ሉዓላዊነታችን ያለንን ቁርጠኝነት የምናድስበትና ከምን ጊዜውም በላይ ኃላፊነታችንን የምንወጣበት ወሳኝ ወቅት ላይ እንገኛለን ብለዋል። አምባሳደሩ አክለውም የሀገራችንን ልማት እና ዕድገት የማይፈልጉ የውስጥና የውጭ ጠላቶቻችን በነጻነታችን እና በሉዓላዊነታችን ላይ የጋረጡብንን ፈተና ለመመከትና ለመቀልበስ ሁላችንም በመናበብና በመደራጀት በተባበረ ክንድ በጋራ ልንቆም ይገባል ብለዋል፡፡

 

17ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዋናው መ/ቤት፣ በሪጅኖች እና በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችም ጭምር በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት የተከበረ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል።

 

//****

ጥቅምት 4 / 2017

አዲስ አበባ

Share this Post