14ኛው የሠንደቅ ዓላማ ቀን በድምቀት ተከበረ

በበዓሉ ላይ የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጥላሁን በቀለ ኢትዮጵያውያን በጋራ ያስመዘገቧቸው ድሎች በርካታና ትውልድም ተሻጋሪ ናቸው ያሉ ሲሆን፣ በራሳቸው ሠንደቅ ዓላማ ስር ነጻነታቸውን ጠብቀው መቆየታቸው ደግሞ በዓለም ጥቁር ህዝቦች ዘንድ እንደስስት ልጅ እንዲታዩ አድርጓቸው ቆይቷል፡፡ በተለይ በቅኝ ግዛት ዘመን ለተገፉ ጥቁር ህዝቦች የነጻነት ምልክትም ተደርገው ተወስደዋል፡፡ ይህ ሁሉ እኛ ኢትዮጵያውያን በአንድ ዓላማ ስር መሰባሰብ በመቻላችን የተገኘ ውጤት ነው ብለዋል፡፡ አክለውም በውስጥና በውጭ ጠላቶቻችን በነጻነታችን እና በሉዓላዊነታችን ላይ የተጋረጠብንን የህልውና አደጋ ለመመከትና ለመቀልበስ ሁላችንም በመናበብና በመደራጀት በተባበረ ክንድ በጋራ ልንቆም ይገባል ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፣ ሠንደቅ ዓላማ የሀገርና የህዝቦች መወከያ ምልክት እንደመሆኑ መጠን ሠንደቅ ዓላማችንን ማክበር፣ መንከባከብና መጠበቅ የምንወደውን ህዝብ፣ ብዙ መስዋዕትነት የተከፈለላትንና የምንሳሳላትን ሀገር ማክበር፣ መንከባከብና መጠበቅ በመሆኑ በየትኛውም ቦታና አጋጣሚ ሁሉ ሠንደቅ ዓላማችንን እናክብር፣ እንንከባከብ፣ እንጠብቅ ብለዋል፡፡

Share this Post