በ9 ወራት ሀገራዊና ተቋማዊ ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት ተካሄደ

በ9 ወራት ሀገራዊና ተቋማዊ ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት ተካሄደ

የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር በዘጠኝ ወራት የሀገር እና የተቋም ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ግንቦት 18/2015 ከዋናው መስሪያ ቤት የስራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ጋር ውይይት አካሄደ።

በሀገራዊ ዕቅዱ በዘጠኝ ወራት ውስጥ በማክሮ ኢኮኖሚ፣ በክፍላተ ኢኮኖሚ፣ በመሠረተ ልማት፣ በሰው ሃብት ልማትና ማህበራዊ ጉዳይ፣ በአስተዳደር፣ በፍትህና የውጭ ጉዳይ ዙሪያ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ቀርበዋል። በተያያዘም አስተዳደሩ በዘጠኝ ወራት ውስጥ የተለያዩ የመረጃ መስጫ መንገዶችን በመጠቀም ለ1.8 ሚሊዮን ተገልጋዮች መረጃ መስጠቱን፣ ለ108,615 የመንግስት ሠራተኞች የመለያ ቁጥር መስጠቱን፣ ለ41,746 ባለመብቶች የጡረታ አበል መወሰኑን፣ ብር 37.61 ቢሊየን የጡረታ መዋጮ መሰብሰቡን፣ ከኢንቨስትመንት 10.4 ቢሊየን ትርፍ መገኘቱን እና ሌሎችም የተገለጹ ሲሆን፣ የህግ ማሻሻያዎች፣ በአሠሪ ተቋማት ላይ የክትትልና የቁጥጥር ስራዎች እንዲሁም የሠራተኞች ድልድልና ስልጠና መከናወኑን በሪፖርቱ ተጠቅሷል።

በመድረኩ ላይ እንደተገለጸው በዘጠኝ ወራት ውስጥ ከተከናወኑት በተጨማሪ በቀሪዎቹ ወራትም የጎደሉ ስራዎችን ተሟልተው ሊሰሩ ይገባል ተብሏል።

ለግማሽ ቀን በተካሄደው የዕቅድ አፈጻጸም የውይይት መድረክ ላይ የአስተዳደሩ አመራሮች፣ የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች ተካፍለዋል።

Share this Post