አስተዳደሩ የ6 ወራት ዕቅድ አፈጻጸሙን ገመገመ
አስተዳደሩ የ6 ወራት ዕቅድ አፈጻጸሙን ገመገመ
የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር በ2018 የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸሙ ላይ ከሪጅን ጽ/ቤቶችና ከዋናው መ/ቤት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ከጥር 13 - 16/2018 ድረስ በአዳማ ከተማ ውይይት አካሄደ።
የአስተዳደሩ ሪጅን ጽ/ቤቶች ባለፉት 6 ወራት በዕቅዳቸው መሠረት ያከናወኗቸውን ተግባሮች በተመለከተ ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን፣ በዚህም የመንግስት ሠራተኞችን በመመዝገብ የማህበራዊ ዋስትና መለያ ቁጥር የመስጠት፣ ለአዲስ የጡረታ ባለመብቶች የጡረታ አበል የመወሰን፣ የመረጃ ተደራሽነትን የማስፋት፣ የጡረታ መዋጮ በትክክል ገቢ መሆኑን የማረጋገጥ፣ የጡረታ ባለመብቶችን መታወቂያ እድሳት የማከናወን እና ሌሎችም የተሰሩ ስራዎችን አቅርበዋል።
በተጨማሪም በግምገማ መድረኩ ላይ የፋይናንስ፣ የግዥ፣ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ የሰው ሃብት አስተዳደርና መሰረታዊ አገልግሎት እንዲሁም የኦዲት የስራ ክፍሎችም ሪፖርታቸውን አቅርበዋል።
በግምገማ መድረኩ ላይ እንደተገለጸው የግማሽ ዓመቱ አፈጻጸም ካለፉት ጊዜያት አንጻር የተሻለ መሆኑንና ይህንን ውጤት በማስጠበቅ የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ ጠንክሮ መስራት ይገባል። ሁሉም ሪጅን ጽ/ቤቶች የሚሰጡትን አገልግሎት ሰው ተኮር የማድረግ፣ የተገልጋዩን ዕርካታ የመለካትና ያሉበትንም ደረጃ የመለየት ስራ ማከናወን ያስፈልጋል።
አስተዳደሩ በ2018 በጀት ዓመት ለማከናወን ካቀዳቸው የመልካም አስተዳደር መርሃ ግብሮች በመጀመሪያው ግማሸ ዓመት የተከናወኑት ለውይይት ቀርበዋል። በዚህ ውይይት እንደተገለጸው በቀጣዮቹ ሁለት ወራት ውስጥ ቀሪ የመልካም አስተዳደር መርሃ ግብሮች መጠናቀቅ አለባቸው። ለዚህም አሠራርን መከተል ያስፈልጋል የተባለ ሲሆን፣ የጡረታ በለመብቶችን መረጃ የማጥራት፣ የጡረታ መታወቂያ ዕድሳትና የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባን የተመለከቱ ስራዎች ትኩረት ይሰጣቸዋል ተብሏል።
ለአራት ተከታታይ ቀናት በተካሄደው የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ላይ የአስተዳደሩ አመራሮች፣ የዋና መ/ቤት የሥራ ኃላፊዎች እና የሪጅን ጽ/ቤቶች ኃላፊዎች ተገኝተዋል።