ጥቅምት 24ን መቸም አንረሳውም

አስተዳደሩ የሰሜን ዕዝ ጥቃት የተፈፀመበትን 2ኛ ዓመት ጥቅምት 24 ቀን አሰበ
የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር አመራርና ሠራተኞች የሀገር መከላከያ ሰሜን ዕዝ በህወሃት ክህደት የተፈፀመበትን 2ኛ አመት “ጥቅምት 24ን መቸም አንረሳውም” ስለኢትዮጵያ የከፈላችሁትን መሰዋትነት መቸም አንረሳውም” በሚል መሪ ቃል ከጠዋቱ 4 ሠዓት ላይ ቀኝ እጃቸውን በግራ ደረታቸው ላይ በማድረግ ለመከላከያ ሠራዊቱ ያላቸውን ክብርና ድጋፍ አሳይተዋል፡፡ 
የአስተዳደሩ ዋና ዳይሬክተር በእለቱ ባስተላለፉት መልዕክት  ሠራዊቱ የተፈጸመበት ግፍ ዘግናኝ መሆኑን ገልጸው ቀኑን ታሪክ የማይረሳው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በእለቱ ለስራ ጉዳይ የተገኙት የሠራዊቱ አባል ጥቅምት 24/2013 ዓ/ም የተፈጸመውን አስነዋሪ ተግባር ካስታወሱ በኋላ አስተዳደሩ ለሠራዊቱ አባላትና ቤተሰቦች በሚሰጠው ቀልጣፋ አገልግሎት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

Share this Post