ኤጀንሲው የ2013 ዓ/ም በጀት አመት አፈፃፀምና 2014 ዓ/ም እቅድ ላይ ውይይት አካሄደ

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳባ ኦሪያ በመክፈቻው እለት እንደተናገሩት 2013 በጀት አመት በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ያለፍንበት አመት ነው እንደ ሀገር ምርጫ፣ የአባይ ግድብ ፣ የሀገራችን የሠላም ሁኔታ ፣ የኑሮ ውድነት እና እንደ አለም አቀፍ ደግሞ ኮቪድ 19 ወረርሽኝ ውስጥ ነበርን ነገር ግን የተሻለ ውጤት አስመዝግበናል ለምሳሌ በሀገር አቀፍ ደረጃ በተደረገው የፀረ ሙስና ትግል ጥሩ ውጤት ካስመዘገቡና ዋንጫ ከተሸለሙ 10 ተቋማት ውስጥ አንዱ የኛ ተቋም ስለሆነ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ እንዳሉት ውዝፍ የጡረታ መዋጮ መኖሩ ፣ ኤሌክትሮኒክስ አገልግሎቶችን የመጠቀም ፕሮጀክት መጓተት፤ የምዝገባና መለያ ቁጥር መስጠትነ እንደ አንድ ስራ መቁጠር፤ የጡረታ አበል መወሰንንና መክፍልን እንደ አንድ ስራ የማየት ነገር መኖሩን በውስንነት የታየ መሆኑን ጠቁመው የውይይቱን መከፈት አብስረዋል፡፡

በእለቱም የሪጅን ጽ/ቤቶችን ጨምሮ አጠቃላይ የኤጀንሲው የ2013 አፈፃፀም እና የ2014 በጀት አመት እቅድ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን በበጀት አመቱ ለ160,000 የመንግስት ሠራተኞች መለያ ቁጥር የመስጠት፤ 153,000 መንግስት ሠራኞችን የመመዝገብ ፤ 1, 232, 194 ማህደሮችን ዲጅታይዝ የማድረግ እና 1 ሪጅን ጽ/ቤት 2 ቅርንጫፍ እና 6 መስክ ጽ/ቤቶች ተከፍተው አገልግሎቱን በቅርበት የመስጠት ሥራ መከናወኑ በዋናነት ከቀረቡት ውስጥ ይጠቀሳሉ፡፡ ከተነሱት ውስነነቶች መካከል በምርመራ ከተገኘው ውዝፍ የጡረታ መዋጮ ለኤጀንሲው ገቢ የተደረገው አናሳ መሆንና የተቋሙ የሪፎርም ስራዎች አለመተግበር የሚሉት ይገኙበታል፡፡

በቀጣይ በጀት አመት ደግሞ በፖስታ ቤት የሚደረጉ ክፍያዎችን ሙሉ በሙሉ ወደ ባንክ የማዞር ፤ ለ3 ሚሊየን ተገልጋዮች በተለያዩ የመረጃ መስጫ ዘዴዎች መረጃን ተደራሽ የማድረግና ሌሎችንም የተቋሙን ዋና ዋና ስራዎች በትኩረት እንደሚሰሩ በእቅድ የተያዘ ሲሆን በተለይ በውስንነቶችና በችግሮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተደረጎ የመፍትሄ አቅጣጫ በመድረኩ ላይ ተነስቷል፡፡ በዚህ መድረክ የሪጀን ጽ/ቤት ሀላፊዎች፤ በዋና መ/ቤት የሚገኙ ዳይሬክተሮች እንዲሁም የተቋሙ ዋና ሀላፊዎች የተሳተፉ ሲሆን በመጨረሻም በአዳማ ከተማ በጡረተኞች ማህበር ግቢ ችግኝ በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል፡፡ ከዚህ በፊት አጠቃላይ የኤጀንሲው ሠራተኞች ጋር በ3 ዙር መወያየቱ የሚታወስ ነው ፡፡

Share this Post