አስተዳደሩ 19ኛውን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በዓል በደማቅ ሁኔታ አከበሩ
አስተዳደሩ 19ኛውን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በዓል በደማቅ ሁኔታ አከበሩ
==============//==============
የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር “ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሃሳብ ለ19ኛ ጊዜ የሚከበረዉን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን ህዳር 23/2017 ዓ.ም ከፍተኛ አመራሮች እና የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ አከብሯል፡፡
በበዓሉ አከባበር የተለያዩ ሁነቶች የተከናወኑ ሲሆን በተለይ ለመወያያ የሚሆን ኅብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓት በኢትዮጵያ፣ ተግዳሮቶቹ እና የመፍትሄ ሀሳቦቹ በሚል ሪዕስ በአስተዳዳሩ የኮርፖሬት ሪሶርስ ማኔጅመንት ዘርፍ ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚ አምባሳደር ምስጋናዉ አድማሱ በኩል ለዉይይት ቀርቧል።
ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚዉ እንዳሉት የበዓሉ አከባበር ዋና ዓላማ በኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች መካከል በብዝኃነት ላይ የተመሰረተ አንድነት ሥር እንዲሰድና እንዲዳብር በማድረግ ህብረ ብሔራዊ አንድነታችንን ለማጎልበት ያለመ ነዉ ብሏል፡፡ አገራችን ኢትዮጵያ የበርካታ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ባለቤት ነች ያሉት ም/ዋና ሥራ አስፈጻማዉ ከዚህ የተነሳ ለዘመናት የቆዩ ከብዙሃነት ጋር ተያይዞ የሚመነጩ ብዙሃ ፍላጎቶችና ጥያቄዎች አሉ ብሏል። እነዚህን ፍላጎቶችና ጥያቄዎች ለመመለስ የሚያስችል ብዙሀነትን ከአንድነት ያስተሳሰረ ህብረ ብሔራዊ ፌደራላዊ ስርዓት ተመስርተዋልም ብሏል።
በኅብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዐታችን የተለያዩ ተግዳረቶች እያጋጠሙ መሆናቸዉን ያመላከቱት ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚዉ በተለይ የፌዴራል ሥርዐቱን በአግባቡ ለመተግበር የሚያስችል ፌዴራላዊ እሳቤ አለመዳበር እና ሥርዐቱን ለመገንባት በአገሪቱ ሊሂቃን መሀከል መሠረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ መግባባት አለመፈጠር መሆኑን እንደምሳሌ ያነሱት ሲሆን ለተግዳረቶቹ ሰፋ ያለ የመፍትሔ ሀሳቦችን አመላክቷል።
በመጨረሻም የዘንድሮውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በዓል ስናከብር መላው የአስተዳደራችን የስራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ለሀገራችን ሠላም እና ብልጽግና ያለንን ቁርጠኝነት በማሳየት ሕብረ ብሔራዊ አንድነታችንን ልናጠናክር እንደሚገባ ሥራ አስፈጻሚዉ አሳስበዋል።
//****
ህዳር 24/2017
አዲስ አበባ