አስተዳደሩ የዘጠኝ ወራት ዕቀድ አፈጻጸሙን ገመገመ

አስተዳደሩ የዘጠኝ ወራት ዕቀድ አፈጻጸሙን ገመገመ

============#####============

የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የበጀት ዓመቱን የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸሙን ከግንቦት 2 – 4/2018 ድረስ በአዳማ ከተማ ገመገመ።

 

የአስተዳደሩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሸጉ ኬሎ እንዳሉት አስተዳደሩ ያስመዘገባቸው ስኬቶች የሁሉም ሠራተኞች ጥረት ውጤት ነው። ይህ ውጤትም ተጠብቆ በቀጣይ የተሻለ አፈጻጸም ለማምጣት መደጋገፍን መሰረት በማድረግ በጋራ መስራት ይጠበቃል። በዚህ መድረክም በዘጠኝ ወራት ውስጥ የተከናወኑ ጠንካራ ስራዎችን በመቀጠል በቀሪ ወራት ውስጥ ልንፈጽማቸው የሚገቡ ቀጣይ ስራዎቻችን ላይ ትኩረት ልንሰጥ ይገባል ብለዋል።

በዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረኩ ላይ በቀረበው ሪፖርት እንደተገለጸው ለ166,252 የመንግስት ሠራተኞች የጡረታ መለያ ቁጥር መሰጠቱንና ለ48,436 አዲስ ጡረታ ለወጡ ባለመብቶች የጡረታ አበል ተወስኗል።

የተቋሙን ስራዎችና አገልግሎቶች ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግም በ8926 ነጻ ስልክ መስመር፣ በህትመት፣ በተለያዩ የአስተዳደሩ የማህበራዊ ሚዲያዎች እና በመገናኛ ብዙሃን መረጃዎችን የማሰራጨት ስራ ተሰርቷል።

በሪፖርቱ እንደተጠቀሰው የክትትልና የቁጥጥር ስራዎችን በተመለከተም በ5,243 መ/ቤቶች ላይ የመዋጮ ገቢ ምርመራ ተደርጓል። በዚህም ውዝፍ የተገኘባቸው ተቋማት ገቢ እንዲያደርጉ ተደርጓል። አመታዊ የጡረታ ባለመብቶች መታወቂያ እድሳት 97% ተከናውኗል።

የተቋሙን የመፈጸም አቅም ለማሳደግም በየደረጃው ለሚገኙ 1,785 አመራሮችና ባለሙያዎች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ስልጠና ተሰጥቷል ተብሏል።

የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታትም አስተዳደሩ የሪፎርም ስራዎች ትግበራን በማጠናከር፣ የአገልግሎት ጥራትን በማሳደግ፣ መረጃዎችን ለሶፍትዌር ዝግጁ በማድረግ እንዲሁም የክፍያ ክትትልና ቁጥጥርን በማጠናከር ላይ ትኩረት በማድረግ በተሰሩ ስራዎች የተገኙ ውጤቶችም ለውይይት ቀርበዋል።

ለሦስት ተከታታይ ቀናት በተካሄደው የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ላይ የአስተዳደሩ አመራሮች፣ የስራ ኃላፊዎች እና የሪጅን ጽ/ቤቶች ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

Share this Post