የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር በተለያዩ ከተሞች ያስገነባቸውን ዘመናዊ ሕንጻዎች በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ

የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር በተለያዩ ከተሞች ያስገነባቸውን ዘመናዊ ሕንጻዎች በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ
የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር የጡረታ ፈንድ አስተማማኝነትን ለማረጋገጥ፣ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመንና ተደራሽነቱን ለማስፋት ያስገነባቸውን ዘመናዊ ሕንጻዎች በዛሬው ዕለት በይፋ አስመርቋል። በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (EBC) በቀጥታ ሥርጭት የታገዘው ይህ የምርቃ ሥነ-ሥርዓት በአዲስ አበባ፣ በባሕር ዳር፣ በሐረር፣ በሀዋሳ እና በሌሎች ከተሞች በደማቅ ሁኔታ ተከናውኗል።
እነዚህ አዳዲስ ሕንጻዎች አስተዳደሩ ለተገልጋዮች የሚሰጠውን አገልግሎት ይበልጥ ፈጣን፣ ቀልጣፋና ምቹ ለማድረግ ከፍተኛ ፋይዳ እንደሚኖራቸው ተገልጿል። የግንባታዎቹ መጠናቀቅ ተቋሙ የጀመረውን የሪፎርም ሥራ ከማጠናከሩ ባለፈ፣ ለተገልጋዮች የሚሰጠውን ምላሽ ጥራት ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ይጠበቃል።

Share this Post