በየደረጃው ለሚገኙ ሴት አመራሮች ስልጠና ተሰጠ

በየደረጃው ለሚገኙ ሴት አመራሮች ስልጠና ተሰጠ
=====//=====
የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር በሁሉም የአስተዳደሩ ጽ/ቤቶች ለሚገኙ ሴት የስራ ኃላፊዎች ሴቶችን ማብቃት/Women Empowerment/ እና የስሜት ብልህነት እና ኮሙኒኬሽን /Emotional Intelligence and Communication/ በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሚያዚያ 1 ቀን 2018 ዓ ም በቪዲዮ ኮንፈረንስ ስልጠና ሰጠ።

በስልጠናው መክፈቻ ላይ የአስተዳደሩ የዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ዘውድነሽ ለገሠ እንዳሉት አስተዳደሩ አገልግሎት አሠጣጡን ፈጣን፣ ቀልጣፋ እና ውጤታማ ለማድረግ የሴቶች አስተዋጽኦ ወሳኝ በመሆኑ በየደረጃው የሚገኙ ሴት የስራ ኃላፊዎች ራሳቸውን ማብቃት ላይ ጠንክረው ሊሰሩ ይገባል ብለዋል። ይህ ስልጠና ሴቶች በሥራቸው፣ በማህበራዊ ህይወታቸው እንዲሁም በኑሯቸው ላይ ለውጥ ማምጣት እንዲችሉ ለማድረግ ታስቦበት የተሰጠ ነው ብለዋል።

በዚህ የስልጠና መድረክ ላይ ሴቶችን ማብቃት በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ በማህበራዊ እና በግል አቅምን የማሳደግ፣ በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ፣ በቴክኖሎጂና በስነ-ልቦና ብቁ ሆኖ ለመገኘት የሚያስችሉ ሃሳቦች ተነስተዋል። ለዚህም የስሜት ብልህነትን ማሳደግ ለመልካም የሥራ ግንኙነትም ሆነ ለማህበራዊ ሕይዎት መጎልበት እጅግ በጣም አስፈላጊ ከመሆኑም ባሻገር ለውጤታማ አመራር መሠረትመሆኑን በስልጠናው ተገልጿል።

በቪዲዮ ኮንፈረንስ በተሰጠው በዚህ ስልጠና በዋናው መ/ቤት እና በሁሉም ሪጅንና ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የሚገኙ ሴት የስራ ኃላፊዎች ተካፍለዋል።

Share this Post