ለጡረታ ባለመብቶች በሙሉ

ለጡረታ ባለመብቶች በሙሉ

======//=====

የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር በተደጋጋሚ በራዲዮ እና በቴሌቪዥን እንዳስታወቀው ከሐምሌ 1/2017 ጀምሮ የ2018 በጀት ዓመት የጡረታ መታወቂያ ዕድሳት በማካሄድ ላይ የሚገኝ መሆኑ ይታወቃል።

 የመታወቂያ ዕድሳት ፕሮግራሙ መስከረም 30/2018 የሚጠናቀቅ በመሆኑ የጡረታ መታወቂያ ያላሳደሳችሁ የጡረታ ባለመብቶች በቀሩት ጥቂት ቀናት በአቅራቢያችሁ በሚገኙ የአስተዳደሩ ጽ/ቤቶች በአካል በመቅረብ እንድታሳድሱ እናሳስባለን።

የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር

Share this Post