የጡረታ ባለመብቶች የብሄራዊ መታወቂያ ምዝገባ ተጀመረ
የጡረታ ባለመብቶች የብሄራዊ መታወቂያ ምዝገባ ተጀመረ
=============//===========
የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የጡረታ ባለመብቶች የብሄራዊ መታወቂያ /National ID/ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ታህሳስ 01 ቀን 2017 ዓ.ም ከኢትዮ ቴሌኮም እና ከጡረታ ከፋይ ባንኮች ጋር በመተባበር የምዝገባ መርሃግብር በይፋ አስጀመረ።
የዚህ ብሄራዊ መታወቂያ ምዝገባ ዋና አላማ የጡረታ ባለመብቶች ቀልጣፋ፣ ፍትሃዊ እና ተደራሽ የጡረታ አገልግሎት ለመስጠት እና ሌሎች የፋይዳ ብሔራዊ መታወቂ የሚሰጠዉን ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ የታሰበ ነዉ፡፡
ምዝገባዉ የተጀመረዉ ታህሳስ 01/2017 ዓ.ም የአስተዳደሩ የኦኘሬሽን ዘርፍ ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጥላሁን በቀለ በተገኙበት በወሊሶ፣ በሰበታ፣ በአለምገና እና በሱሉልታ ከተሞች ናቸዉ፡፡
በጡረታ ባለመብቶቹ ላይ አላስፈላጊ መጉላላት እና መጨናነቅ እንዳይፈጥር በማሰብ ከብሔራዊ መታወቂያ ጎን ለጎን የጡረታ አበል መታወቂያ ዕድሳት እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን ለሚቀጥሉት ተከታታይ ወራቶች በሁሉም ሪጅኖች እና ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የሚካሄድ መሆኑ የተገለፀ ስሆን ባለመብቶች ወደ ምዝገባ ጣቢያ በመሄድ ተመዝግበው መታወቂያቸዉን እንድወስዱ አሳስበዋል።
መረሃግብሩ ስጠናቀቅ “ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025”ን እውን ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረዉ ይገመታል።
//****
ታህሳስ 03/2017
አዲስ አበባ