ዓለም አቀፍ የኤድስ እና የጸረ ጾታ ጥቃት ቀን ተከበረ
ዓለም አቀፍ የኤድስ እና የጸረ ጾታ ጥቃት ቀን ተከበረ
==========//===========
የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር አመራሮችና ሠራተኞች አለም አቀፍ ኤድስ ቀን እና የነጭ ሪባን/የጸረ ጾታ ጥቃት ቀናት ማጠቃለያ ህዳር 27/2017 በድምቀት አከበሩ።
በበዓሉ አከባበር ላይ የተገኙት የአስተዳደሩ የኮርፖሬት ሪሶርስ ማኔጅመንት ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ምስጋናዉ አድማሱ እንዳሉት ኤች አይ ቪ ኤድስ ገዳይነቱ አሁንም ድረስ እንደቀጠለ መሆኑን ገልፀዉ የቫይረሱ ስርጭት ግን እየቀነሰ መሆኑን ቢነገርም ውጤቱ አመርቂ አይደለም ብለዋል።
አስተዳደሩም የቫይረሱን ስርጭት አሳሳቢነት ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የኤች አይቪ/ኤድስ ጉዳይን በዕቅዱ ውስጥ ያካተተ ሲሆን፣ በዘርፉ የአመራሩንና ፈጻሚውን ግንዛቤ ለማሳደግም ይህን መሠል የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች እንዲዘጋጁና ሠራተኞችም በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ የኤች.አይ.ቪ ምርመራ እንዲያደርጉ እያበረታታ ይገኛል ብለዋል፡፡ የኤች አይ ቪ/ኤድስ ፈንድን ለማጠናከርም ከአስተዳደሩ ሠራተኞች በየወሩ በአማካይ ብር 9,649 ያህል የሚሰበሰብ ሲሆን፣ ቫይረሱ በደማቸው ለሚገኝ 22 የአስተዳደሩ ሠራተኞች ከዚህ ገንዘብ በየወሩ ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡
አምባሳደሩ አክለውም በሴቶች ላይ የሚቃጡ ጥቃቶችን መከላከል የሁላችንም ኃላፊነት ነው፤ ከስርዓተ ፆታ ጋር በተያያዘ በስራም ሆነ በመኖሪያችን አካባቢ የሚታዩ የተዛቡ አመለካከቶችን ለመከላከል ግንባር ቀደም ተሳታፊ ልንሆን እንደሚገባም ጠቁመዋል።
አለም አቀፍ ኤድስ ቀን በሃገራችን ለ36ኛ ጊዜ “ሰብዓዊ መብትን ያከበረ የኤች. አይ. ቪ. አገልግሎት ለሁሉም!” እንዲሁም የነጭ ሪባን/የጸረ ጾታ ጥቃት ቀን፤ ለ19ኛ ጊዜ “የሴቷ ጥቃት የእኔም ነው፤ ዝም አልልም - እኔ ለእሷ!” በሚሉ መሪ ሃሳቦች የተከበሩ ሲሆን፣ በተጨማሪም በዕለቱ የፀረ-ሙስና ቀን ለ20ኛ ጊዜ በሀገራችን “ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፣ የነገን ስብዕና ይገነባል!” በሚል መሪ ሃሳብ ተከብሮ ውሏል።
በበዓሉ ላይ የዋናው መስሪያ ቤት እና የመሃል ሪጅን ጽ/ቤት አመራሮችና ሠራተኞች ተገኝተዋል።
//****
ህዳር 30/2017
አዲስ አበባ