የአስተዳደሩ አመራሮች እና ሰራተኞች "የህልም ጉልበት ለእምርታዊ እድገት" በሚል ርዕስ በተዘጋጀዉ ሰነድ ላይ ዉይይት አካሄዱ
የአስተዳደሩ አመራሮች እና ሰራተኞች "የህልም ጉልበት ለእምርታዊ እድገት" በሚል ርዕስ በተዘጋጀዉ ሰነድ ላይ ዉይይት አካሄዱ
============//============
የመንግሰት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር አመራሮች እና ሠራተኞች "የህልም ጉልበት ለእምርታዊ እድገት" በሚል ርዕሰ ጉዳይ በተዘጋጀ ሰነድ ላይ ህዳር 06/2017 ውይይት አካሄዱ፡፡
የዉይይት ሰነዱን ያቀረቡት የአስተዳዳሩ ኮርፖሬት ሪሶርስ ማኔጅመንት ዘርፍ ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚ አምባሳደር ምስጋናዉ አድማሱ ሲሆን መንግስት የሚያስቀምጣቸው የልማት እቅዶችና ህልሞች በመንግሥት ሰራተኛው ርብርብ የሚሳካ በመሆኑ የጋራ ግንዛቤ መያዝና መፈፀም እንደሚገባ አመላክቷል።
ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚዉ እንዳሉት አሁን ኢትዮጵያ ያላት መንግስት የልዕልና ህልም ያለዉ መንግስት መሆኑን ያመላከቱ ሲሆን የልማት እቅዶችና ህልሞች እንዲሳኩ የሁሉም ዜጎች ተሳትፎና ርብርብ አስፈላጊ ነዉ ብሏል፡፡ የጋራ ሀገር እንዲኖረን ሁሉምን ዜጋ የጋራ የሚያደርገንን ብሄራዊ ትርክቶች ላይ በማተኮር መስራት እንደሚገባ ሥራ አስፈጻሚዉ ጨምረው ገልጸዋል፡፡
በተለይም ከዚህ በፊት ከነበረዉን የግብርና መር ኢኮኖሚ ወደ የብዙሃ መር ኢኮኖሚ ሽግግር ከጫፍ እንድደርስ ተግቶ መሥራት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
የመድረኩ ተሳታፊዎችም ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ ፖለቲካዊ እንዲሁም ቀጠናዊ ጉዳዮችን አንስተው ተወያይተዋል፡፡
በዚህ በተዘጋጀዉ የዉይይት መድረክ ላይ የተቋሙን አመራሮች እና ሰራተኞች ተካፍለዋል።
//****
ህዳር 06/2017
አዲስ አበባ