የመንግስት የመቶ ቀን የሪፎርምና ዋና ዋና የኢኮኖሚ አፈጻጸም ላይ ውይይት ተካሄደ

የመንግስት የመቶ ቀን የሪፎርምና ዋና ዋና የኢኮኖሚ አፈጻጸም ላይ ውይይት ተካሄደ

የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የስራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በመንግስት የ100 ቀናት ዕቅድ አፈጻጸም እና በተቋሙ የሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ጥቅምት 18/2017 በዋናው መ/ቤት ውይይት አካሄዱ።

በመድረኩ ላይ እንደተገለጸው በመንግስት የመቶ ቀናት አፈጻጸም ውስጥ የተከናወኑ ተግባራትና የተገኙ ውጤቶችን በተመለከተ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፣ የሪፎርሙ ተጠባቂ ፋይዳዎች፣ የግብር ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፋይዳዎች፣ በዕዳ አስተዳደር ላይ ያለ አፈጻጸም፣ የተረጋጋ የማክሪ ኢኮኖሚ፣ የዘርፎች ምርታማነትና ተወዳዳሪነት የሚሉና ሌሎችም የቀረቡ ሲሆን፣ በዋና ዋና ፕሮጀክቶች አፈጻጸምም የህዳሴ ግድብ አሁን ያለበት ደረጃ 97.6 በመቶ መድረሱን፣ የአዲስና የፍጥነት መንገዶች ግንባታ በመከናወን ላይ መሆኑን ተገለጿል። በቀጣይም የወጪ ንግድን በተመለከተ በቅንጅት የሚሰራ መሆኑን፣ የቁጥጥር ስራዎችም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ፣ ክልሎችን ወደ ኤሌክትሮኒክስ ፋይናንስ ስርዓት የማምጣትና የተጣጣመ የታክስና ፋይናንስ ስርዓት ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ናቸው ተብሏል።

በተያያዘም የአስተዳደሩ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለውይይት የቀረበ ሲሆን፣ ለ32,741 (102%) የመንግስት ሠራተኞች የማህበራዊ ዋስትና መለያ ቁጥር መሰጠቱን፣ ለ18,967 አዳዲስ ባለመብቶች የጡረታ አበል መወሰኑን፣ ባንክ ባልተከፈተባቸው አካባቢዎች ለ5862 ባለመብቶች የጡረታ አበል በመስክ አገልግሎት ክፍያ መፈጸሙን፣ ከ875 የመንግስት መ/ቤቶች ለተሳተፉ 3,519 ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሰጠቱን፣ ብር 9.94 ቢሊ. የጡረታ መዋጮ ገቢ መሰብሰቡንና ሌሎችም ተከናውነዋል ተብሏል።

 

 

Share this Post