የመንግስት ሠራተኞች ማኀበራዊ ዋስትና አስተዳደር የሥራ ውል ስምምነት ተፈራረመ

የመንግስት ሠራተኞች ማኀበራዊ ዋስትና አስተዳደር የሥራ ውል ስምምነት ተፈራረመ

=============//===========

አዲስ አበባ፡ መስከረም 3/2017 ዓ.ም፡ የመንግስት ሠራተኞች ማኀበራዊ ዋስትና አስተዳደር  ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር  ጋር የሥራ ውል ስምምነት ተፈራረሙ።

 

ስምምነቱ ዌብ ላይ መሰረት ያደረግ የተቀናጀ ብሔራዊ የማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ስርዓትን ለመዘርጋት የሚያስችል ሲሆን ስራዉ በውስጡ-7 ንዑስ ሲስተሞች የያዘ መሆኑን ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ድህረገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

 

ትግበራዉ ሲጠናቀቅ የጡረታ ምዝገባን፣ የጡረታ መዋጮ ክፍያን፣ የጡረታ ተጠቃሚነትን እና ሌሎች ስርዓቶችን በማቀናጀት እና በቴክኖሎጂ በማዘመን ሥራን የሚያቀላጥፍ ይሆናል ተብሎ ይገመታል።

 

ከሶስት አመት በፊት ጀምሮ አስተዳደሩን ብቃት ባለዉ የሰዉ ሀይል ለማደራጀትና አሰራሮችን በቴክኖሎጂ ለማዘመን ሰፊ የሪፎርም ሥራዎች ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል ።

 

://***

Share this Post