የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ከመንግስት አሠሪ መስሪያ ቤቶች ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ

የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ከመንግስት አሠሪ መስሪያ ቤቶች ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ

=========//==============

የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ከማስረጃ አያያዝ እና ከጡረታ መዋጮ ገቢ አሰባሰብ ጋር በተያያዘ ከመንግስት አሠሪ መስሪያ ቤቶች የስራ ኃላፊዎች ጋር ጳጉሜ 4 ቀን 2016 የምክክር መድረክ አካሄደ።

 

በመድረኩ ላይ የተገኙት በአስተዳደሩ የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጥላሁን በቀለ እንዳሉት ተቋሙ የተለያዩ የሪፎርም ስራዎችን በማከናወን አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን በርካታ ጥረቶችን በማድረግ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ የዚህ መድረክ አላማም በተቋሙ የሪፎርም ስራዎችና በማስረጃ አያያዝ ላይ ግንዛቤ መፍጠር ነው ብለዋል። የአዋጅ ማሻሻያ ከተደረገ በኋላ ከጡረታ መዋጮ ገቢ አሰባሰብ ጋር በተያያዘ የአስተዳደሩ አፈጻጸም መሻሻል የታየበት ሲሆን፣ በቀጣይም ከተለያዩ ተቋማት ጋር ስራዎችን በጋራ ለመስራት ዕቅድ የተያዘ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚዉ እንደገለፁት ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን እና ከማዕከላዊ ስታትስቲክስ አገልግሎት ጋር በጋራ በመሆን የመንግስት ሠራተኞችን ቆጠራ ለማካሄድ የታቀደ ሲሆን፣ አሠሪ መስሪያ ቤቶችም ትክክለኛ መረጃ በመስጠት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

 

በምክክር መድረኩ ላይ በጡረታ አዋጅ ማስፈጸሚያ መመሪያዎች፣ በምዝገባና የጡረታ አበል ውሳኔ የመረጃ አቀራረብ ላይ እንዲሁም በጡረታ መዋጮ ገቢ አሠባሰብ ላይ ትኩረት ያደረጉ ገለጻዎች ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል።

 

በዋናው መስሪያ ቤት በተካሄደው በዚህ የውይይት መድረክ ላይ ከ72 የፌዴራል አሠሪ መስሪያ ቤቶች የተገኙ 144 የሰው ሃብት እና የፋይናንስ የስራ ኃላፊዎች ተካፍለዋል።

://***

ጳጉሜ 4/2016 ዓ/ም

አዲስ አበባ

Share this Post