የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት የአስተዳደሩን የስራ እንቅስቃሴ ጎበኙ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት የአስተዳደሩን የስራ እንቅስቃሴ ጎበኙ

በኢፌዲሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት የአስተዳደሩን አጠቃላይ የስራ እንቀስቃሴ ታህሳስ 01 ቀን 2016 በዋናው መስሪያ ቤት በመገኘት የስራ ጉብኝት አደረጉ፡፡

የቋሚ ኮሚቴው አባላት የአስተዳደሩን የተለያዩ የስራ ክፍሎች ጎብኝተዋል። በጉብኝቱም የየክፍሎቹን የስራ እንቅስቃሴ እና የተቋሙን በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት አሠጣጥ በተመለከተ ለቋሚ ኮሚቴው አባላት ገለፃ የተደረገ ሲሆን፣ ላነሷቸው ጥያቄዎችም ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው አባላት አስተዳደሩ በአዲስ አበባ ከተማ ፒያሳ አካባቢ ያስገነባውን ዋስትና ሜጋ ኮሜርሺያል ሕንጻንም የጎበኙ ሲሆን፣ ይህ በጎ ጅምርም ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።

የአስተዳደሩ አመራሮችም ቋሚ ኮሚቴው የሰጠውን ግብዓት በመጠቀም የተቋሙን አሠራር ይበልጥ ለማሻሻል እንደሚጠቀሙበት ገልጸዋል፡፡

Share this Post