የሠንደቅ ዓላማ ቀን ተከበረ

የሠንደቅ ዓላማ ቀን ተከበረ

የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር አመራሮችና ሠራተኞች ለ16ኛ ጊዜ የተከበረውን የሠንደቅ ዓላማ ቀን ጥቅምት 5/2016 ‘የሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ ለሕብረ-ብሔራዊ አንድነታችንና ለሉዓላዊነታችን ዋስትና ነው!” በሚል መሪ ሃሳብ አከበሩ።

የአስተዳደሩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዳባ ኦሪያ በአከባበር ስነ-ስርዓቱ ላይ እንዳሉት ሠንደቅ ዓላማ የብሔራዊ አንድነት መገለጫ፤ ዜጎች አገራዊ ፍቅርና ብሔራዊ ስሜታቸውን የሚገልፁበት፤ ታሪካዊ ትስስርና ስነ-ልቦናዊ አንድነት የሚንፀበረቅበት የአንድነትና ህብረት ዓርማና ምልክት ነው፡፡ በመሆኑም በየትኛውም ቦታና አጋጣሚ ሁሉ ሠንደቅ ዓላማችንን እናክብር፣ እንንከባከብ፣ እንጠብቅ ብለዋል።

Share this Post