በየደረጃው ለሚገኙ የስራ ኃላፊዎች ስልጠና ተሰጠ

በየደረጃው ለሚገኙ የስራ ኃላፊዎች ስልጠና ተሰጠ

የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር በየደረጃው ለሚገኙ የተቋሙ የስራ ኃላፊዎች ቢሾፍቱ በሚገኘው የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ከነሐሴ 06 – 18/2015 ድረስ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ስልጠና ሰጠ።

አስተዳደሩ በ2015 ባካሄደው የሰራተኞች ምደባ በየደረጃው ወደ ኃላፊነት የመጡ ሠራተኞችን አቅም ለመገንባት ባዘጋጀው የስልጠና መድረክ ላይ Mindset and Change Management, Political economy landscape, Social Protection and Security, Ethical leadership, Service delivery and good governance, Instuitonal reform and implementation, Communication, እና Management and Leadership ላይ ትኩረት ያደረጉ ስልጠናዎች ተሰጥተዋል። በተጨማሪም በመዋጮ ገቢ አሠባሰብ፣ በጡረታ አፈጻጸም መመሪያ እና በተቋሙ ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ላይ ውይይት ተካሂዷል።

በስልጠና መድረኩ ላይ እንደተገለጸው ራስን በማብቃት እና የቡድን ስራን በማጠናከር በኩል በርትቶ መስራት ይጠበቃል የተባለ ሲሆን፣ ስልጠናውም ለዚህ ከፍ ያለ እገዛ ይኖረዋል ተብሏል። ስራን እና ተቋምን ለመቀየር በቅድሚያ መሪዎች ራሳቸውን መቀየር ስለሚገባቸው፣ በተሰጡት ስልጠናዎች ከሁሉም ውጤት እንደሚጠበቅ እና በአሠራርና በኮሙዩኒኬሽን መለወጥና መሻሻል ይገባል፡፡

የስልጠናው ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት የተሰጡ ስልጠናዎች አስፈላጊ እና በአሰራር ላይ ለውጥ ማምጣት እንዲችሉ የሚያደርጉ ናቸው ያሉ ሲሆን፣ በርዕሰ ጉዳዮቹ ላይ ከፍ ያለ ዕውቀት ባላቸው ግለሰቦች የተሰጠ መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።

ቢሾፍቱ በሚገኘው የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት በተካሄደው በዚህ የስልጠና መድረክ ላይ የተቋሙን አመራሮች ጨምሮ ወንድ 91፣ ሴት 26 በአጠቃላይ 117 በየደረጃው የሚገኙ የዋናው መ/ቤት፣ የሪጅን እና ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የስራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።

Share this Post