አስተዳደሩ ለተለያየ አገልግሎት የሚውሉ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ

አስተዳደሩ ለተለያየ አገልግሎት የሚውሉ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ

የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ለቢሮ እና ለሕጻናት ማቆያ ማዕከል የሚያገለግሉ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ለቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አስተዳደር ሐምሌ 21 ቀን 2015 ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉ ወረዳው ያለበትን የቁሳቁስ እጥረት በመቅረፍ አገልግሎት አሠጣጡ እንዲሻሻል እና የሕጻናት ማቆያ ማዕከል እንዲቋቋም የሚያግዝ ነው።

ለወረዳው ከተሰጡ ቁሳቁሶች መካከል ኮምፒዩተሮች፣ ፕሪንተር፣ ጠረጴዛዎች፣ ወንበሮች፣ የሕጻናት አልጋ፣ ሼልፍ እና ሌሎችም ይገኙበታል።

Share this Post