አስተዳደሩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጠ

አስተዳደሩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጠ

 

የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር በጡረታ አዋጁ እና አፈጻጸሙ ዙሪያ  ታህሳስ 6/2015 ዓ/ም ለአሰሪ መ/ቤቶች የግማሽ ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ በራስ ሆቴል ሰጥቷል፡፡

የአስተዳደሩ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጥላሁን በቀለ መድረኩን በንግግር ሲከፍቱ እንደተናገሩት የግንዛቤ ማስጨበጫው ዋና አላማ በቀርቡ የወጣው የጡረታ አዋጅ ቁጥር 1267 በፊት ከነበሩት የጡረታ አዋጆች ምን ምን ነገሮችን አሻሻለ የሚሉትን ዋና ዋና ሀሳቦች ለማስተላለፍ ሲሆን በተጨማሪም በማስረጃ አያያዝና ገቢ አሰባሰብ ላይ የጋራ ግንዛቤ ለማስያዝ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አዋጁ በዋናነት የጡረታ ፈንዱን ዘላቂነት ለማረጋገጥ ተቋሙ በተመረጡ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ መሠማራት እንዲችል ለማድረግ፤ የጡረታ መለያ ቁጥር በብሄራዊ መታወቂያ እንዲሆን ለማስቻል እና  የቴክኖሎጅ ሽግግርን ማሳለጥ እንዲቻል ማድረጉንም ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አክለዋል፡፡

የግንዛቤ ማስጨበጫው ያተኮረው በመንግስት ሠራተኞች ምዝገባ፤ በመዋጮ ገቢ አሰባሰብ፤ በጡረታ አበል ውሳኔ እና ማስረጃዎች ላይ ሲሆን የምዝገባና አበል መወሰኛ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሲሳይ እምሩ፣ የመዋጮ ገቢ ዳይሬክቶሬት አቶ ሙሉብርሃን ካህሳይ እና የአበል ውሳኔ ቡድን መሪ አቶ ሸዋንግዛው ታየወርቅ ገለጻ አድርገዋል፡፡

በቀረበው ገለጻ ላይ የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከተሳታፊዎች የተነሱ ሲሆን ከተነሱት ሀሳቦች ውስጥ ፡- የልደት ዘመን አያያዝ፣ የኮንትራት   አገልግሎት  እና  የጡረታ አበል ስሌት ሬት  በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ በተነሱት ሀሳቦችና ጥያቄዎች ላይም ሰፊ ምላሽና ማብራሪያ ከመድረክ  ተሰጥቷል፡፡

በዚህ መድረክ ከተለያየ አሰሪ መ/ቤቶች የተውጣጡ የሰው ሀብትና የፋይናንስ ሀላፊዎችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡

 

Share this Post