በአስተዳደሩ የሰንደቅ አላማ ቀን ተከበረ

በአስተዳደሩ የሰንደቅ አላማ ቀን ተከበረ

የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር አመራርና ሠራተኞች 15ኛውን የሠንደቅ አላማ ቀን “ሠንደቅ አላማችን፣ የብዝሃነታችን መገለጫ ፣የሉዓላዊነታችን ምሰሶ ነው!” በሚል መሪ ቃል ጥቅምት 7/2015 ዓ/ም በተቋሙ ቅጥር ግቢ አክበረዋል፡፡

የአስተዳደሩ ምክትል ዋና ዳይሬከተር አቶ ጥላሁን በቀለ ባደረጉት ንግግር የዘንድሮን የሠንደቅ አላማ ቀን የምናከብረው በብዙ ፈተና ውስጥ ሆነን ነው ፡፡ ካሉ በኋዋላ ሀገራችን አሁን የተጋረጡባትን ፈተናዎች ሁሉ አልፋ ክብሯን እና ነጻነቷን ጠብቃ የብልጽግና ጉዞዋን ለማስቀጠል ጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን ያለንን ክብርና ድጋፍ የምናረጋግጥበትና ቃላችንን የምናድስበገት ወቅት ላይ እንገኛለን፡፡ ያሉ ሲሆን መከላከያ ሠራዊታችን የሀገራችንን ሉዓላዊነት ለማስከበር ለሚከፍለው የህይወት መሰዋትነት ያለንን ከፍ ያለ ክብር በመግለጽ ከጎኑ መቆማቸንን በድጋሚ እናረጋግጣለን፡፡ በተጨማሪም  የሀገርና ህዝባችን መወከያ ምልክት የሆነውን ሠንደቅ አላማ የማክበር፣  የመጠበቅና የመንከባከብ ሀላፊነት አለብን በማለት አክለዋል፡፡

Share this Post