የአስተዳደሩ አመታዊ የዕቅድ አፈጻጸም የግምገማ መድረክ ተካሄደ

በመድረኩ ላይ ለውይይት በቀረበው ሪፖርት እንደተገለጸው፣ አስተዳደሩ በበጀት ዓመቱ ካከናወናቸው ዋና ዋና ተግባሮች ውስጥ የ222,918 የጡረታ ባለመብቶች ክፍያ ወደ ባንኮች መዘዋወሩ፣ ለ153,091 የመንግስት ሠራተኘች የጡረታ መለያ ቁጥር መሰጠቱ፣ ለ41,887 አዲስ ባለመብቶች የጡረታ አበል መወሰኑን፣ በ11 ወራት ውስጥ ብር 37.61 ቢሊየን የጡረታ መዋጮ ገቢ መሰብሰቡን፣ በአራት የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ በመሳተፍ ብር 9.97 ቢሊየን ገቢ መገኘቱን፣ በ4,874 መዋጮ ከፋይና ሰብሳቢ መ/ቤቶች ላይ የገቢ ምርመራ በማድረግ በወቅቱ ያልገባ ብር 3.70 ቢሊየን ውዝፍ መገኘቱንና ከተገኘው ውስጥ ብር 1.64 ቢሊየን ገቢ መደረጉን፣ በ24 የአስተዳደሩ ጽ/ቤቶች የፋይናንስ፣ የንብረትና የክዋኔ ኦዲት መከናወኑን፣ ከሪፎርም ተግባራት አኳያ የተሻሻለው የመንግስት ሠራተኞች ጡረታ አዋጅ መጽደቁን፣ የሀብት ማሳወቂያ ማስመዝገቢያ እና የጥቆማ መቀበያ መተግበሪያ ሥራ ላይ እንዲውል መደረጉን፣ የሀብት ማሳወቅ ምዝገባ መመሪያ መሠረት የ2,111 ሠራተኞችን በዲጂታል መንገድ የሃብት ምዝገባ መከናወኑን፣ አሰራርን ለማሻሻል የኤሌክትሮኒክ (e-service) ወረቀት አልባ አሰራር (e-office) በመጠቀም አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን፣ የንብረት ምዝገባ፣ ስርጭት፣ ቆጠራ፣ የነዳጅ ልኬት፣ እንዲሁም አገልግሎት የማይሰጡ ንብረቶች እንዲወገዱ መደረጉን፣ የሰው ኃይል የመፈጸም አቅምን ለማሳደግ ለ2,045 ሠራተኞች የሥራ ላይ ሥልጠና መሠጠቱን የሚሉት እና ሌሎችም ተግባሮች የቀረቡ ሲሆን፣ ውይይትም ተካሂዶባቸዋል፡፡ በተጨማሪም ገቢ ያልሆነ ውዝፍ የጡረታ መዋጮ መኖሩ እና የፕሮጀክቶች አፈጻጸም በታሰበው ጊዜ አለመጠናቀቁ ደግሞ በሪፖርቱ በክፍተትነት የተጠቀሱ ናቸው፡፡

ለአራት ተከታታይ ቀናት በተካሄደው የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ላይ የዋናው መ/ቤት የስራ ክፍሎች እና የሪጅን ጽ/ቤቶችም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን፣ በረቂቅ የጡረታ አዋጅ ማስፈጸሚያ መመሪያ እና ማኑዋል ላይም ውይይት ተካሂዷል፡፡

በዋናው መ/ቤት በተካሄደው የውይይት መድረክ ላይ የተቋሙ አመራሮች፣ የስራ ሂደት ኃላፊዎች፣ እና የሪጅን ጽ/ቤቶች ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

Share this Post