የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የአቅመ ደካማ ቤት እድሳት ስራ አስጀመረ

የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የአቅመ ደካማ ቤት እድሳት ስራ አስጀመረ

 

የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር  ከአዲስ አበባ ከተማ አስደዳር ጋር በመተባበር  የሚካሄደውን የአቅመ ደካማ ቤት እድሳት ፕሮግራም የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጥላሁን በቀለ ሐምሌ 30/2014 ዓ/ም በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 በመገኘት የአቅመ ደካማ ቤት እድሳት ስራውን አስጀምረዋል::  ምክትል ዋና ዳይሬክትሩ ስራውን ሲያስጀምሩ እንደገለፁት በዛሬው እለት የ 4 እናትና አባቶቻችንን ቤት ለማደስ የጀመርን ሲሆን በመ/ቤቱ በኩልም በጀት መመደቡን ገልጸው በተቀመጠው ጊዜ ለመጨረስ ጥረት እናደርጋለን ሲሉ አክለዋል፡፡  እሳቸውን ጨምሮ ሌሎች የተቋሙ ሀላፊዎችና ሠራተኞችም ተሳትፈዋል፡፡

Share this Post