በአስተዳደሩ ማዕድ የማጋራት ፕሮግራም ተካሄደ

በመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ዝቅተኛ ደመወዝ ላላቸው ሠራተኞች ሐምሌ 1 / 2014 ዓ/ም ማዕድ የማጋራት መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡ 

የአስተዳደሩ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳባ ኦሪያ በእለቱ ተገኝተው ለድጋፉ ተጠቃሚዎች  እንዳሉት እኛ ጤነኞች በመሆናችን የተሻልን ነን ነገር ግን የተቋማችን ጡረተኛ የሆኑ እጅግ በጣም የሚያሳዝን የኑሮ ሁኔታ ላይ ያሉ 4 ግለሰቦችን ተለይተው ቤታቸው በተቋሙ እየታደሰላቸው መሆኑን ገልጸው ከዚህ ማዕድም የሚጋሩ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

በአስተዳደሩ የሰው ሃብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ መሰረት በሻህ እንዳሉት ዝቅተኛ ደመወዝ ያላቸው የኤጀንሲው ሠራተኞች  የኑሮ ውድነቱን መቋቋም እንዲችሉ ለ199 ሠራተኞች  እና በጣም ዝቅተኛ የጡረታ አበል ተከፋይ ለሆኑና ተቋሙም ቤታቸውን እያደሰላቸው ለሚገኙ  ጡረተኞችም በማዕድ ማጋራት መርሃ ግብሩ እንዲደገፉ ተደርገዋል ያሉ ሲሆን፣ በአጠቃላይ ከዋና መ/ቤት  ፤ ከመሃል ሪጅን ጽ/ቤት፣ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ሪጅን ጽ/ቤት ደመወዛቸው 3500 በታች ለሆኑ 199 ሠራተኞች  እና 4 በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ጡረተኞች  በድጋፉ መካተታቸውን የገለፁት  ዳይሬክተሯ በነፍስ ወከፍ 25 ኪሎ ዱቄት፣  10 ኪሎ ሩዝ፣ 5 ኪሎ መካሮኒ እና 5 እሽግ ፓስታ ድጋፍ መደረጉን ተናግረልዋል፡፡

የድጋፉ የገንዘብ ምንጭ በዋናው መ/ቤት  ፣ በመሃል ሪጅን ጽ/ቤት እና  በአዲስ አበባ ሪጅን ጽ/ቤት በሚገኙ የሠራተኛ ክበቦች የተገኘ መሆኑን ገልጸው ለዚህም 598,875.00 (አምስት መቶ ዘጠና ስምንት ሽህ ስምንት መቶ ሰባ አምስት ብር) ወጭ  አድርገዋል ያሉት ዳይሬክተሯ፣ ይህ ድጋፍ  ከቪድ 19 ከገባ ጀምሮ ያሁኑ ለ3ኛጊዜ የተደረገ ሲሆን ወቅታዊ የሆነው የኑሮ ውድነት በሠራተኞች ላይ የሚያሳድረውን ጫና ለመቀነስ የታሰበ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

Share this Post