አዲሱ የመንግስትና የግል ሰራተኞች የጡረታ አዋጅ ሲብራራ

የመንግስት ሰራተኞች የጡረታ አዋጅ ለማህበራዊ ፍትህ፣ ለኢንደስትሪ፣ ሰላም፣ ለድህነት ቅነሳ፣ ለምርታማነትና ልማት ጉልህ አስተዋጽኦ ያለው እና የማህበራዊ መድህን ስርዓትን ለማስፋፋት ወሳኝ ሚና ይጫወታል ተብሏል።

አዲሱ አዋጅ የጡረታ እድሜን ጣራ 60 ዓመት እንዲሆን እንዲሁም ጡረተኛው በህይወት ሳለ የሚያገኘው የጡረታ መጠን ሲያልፍ የትዳር አጋር 50 በመቶ የጡረታው ተጠቃሚ መሆንን ይፈቅዳል።

የፖሊስና መከላከያ መዋጮ ከግለሰቡ የሚደረገው ሌሎች የግልና የመንግስት ሰራተኞች እንደሚያዋጡት 7 በመቶ ሆኖ ከመንግስት አካል የሚደረግለት መዋጮ ግን ወደ 33 በመቶ ከፍ እንዲል ተደርጓል።

ሌላው በምክር ቤቱ የጸደቀው የግል ድርጅቶች ሰራተኞች ጡረታ አዋጅ ሲሆን ፥ ይኸውም በድርጅቶች ምክንያት ሳይዋጣ የቀረን ገንዘብ በሶስት ወር ውስጥ ገቢ ካልተደረገ በቀጥታ ድርጅቱ ካለው ማንኛውም የባንክ አካውንት ገቢ እንዲደረግበት የሚያስገድድ ነው።

የግል ድርጅት ባለቤቶች በድርጅቱ ሰራተኛ ሆነው በጡረታ ማዕቀፉ ውስጥ እንዳይገቡም አዋጁ አግዷል።

ከአስር ዓመት በላይ ያገለገለ ሰራተኛ እድሜው ለጡረታ በሚደርስበት ጊዜ የእድሜ ልክ ጡረታ ተከፋይ እንዲሆንም አዋጁ ይፈቅዳል።

የሚሰበሰበው የጡረታ መዋጮም ወደ ኢንቨስትመንት በማስገባት ገቢን በማሳደግ ለጡረተኞች የክፍያ ማሻሻያ የሚያደርግበትን እድልም የሚፈጥር ነው።

አንድ አሰሪ የግል ድርጅት ፍቃዱን በሚያድስበት ጊዜ የሰራተኞቹን መዋጮ ካላስገባ ፍቃዱ የሚይታደስበት አስገዳጅ አንቀጽም ተካቷል።

Share this Post