የአስተዳደሩ ሠራተኞች “የኢትዮ-ግሪን ሞቢሊቲ 2024” ኤግዝብሽንና ሲምፖዚየም ጉብኝት አካሄዱ
የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር “የኢትዮ-ግሪን ሞቢሊቲ 2024” በሚል ያዘጋጀውን ዓለም አቀፍ ኤግዝብሽንና ሲምፖዚየም ህዳር 19 ቀን 2017 ጎበኙ።
ሁጅዋን ቀላል ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ በተዘጋጀው በዚህ ኤግዝብሽንና ሲምፖዚየም የኤሌክትሪክና ታዳሽ ኃይል ተሽከርካሪዎች እንዲሁም ተያያዥ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለዕይታ የቀረቡ ሲሆን፣ ዓላማውም ሀገራችን ለአየር ንብረት ለዉጥ የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ሀሳብ አመንጪነት እና አመራር ሰጪነት በከፍተኛ ትኩረት እየተሰሩ ካሉ ሥራዎች አንዱ ሲሆን የኤሌክትሪክ እና ታዳሽ ኃይል ተሸከርካሪዎች ዙሪያ በአገራችን ያለዉ ግንዛቤ በማሳደግ የአረንጓዴ ትራንስፖርት ስርዓትን ለመገንባት የሚደረገዉ አገራዊ ጥረት ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ተገልጸዋል፡፡
በዚህ ኤግዝብሽንና ሲምፖዚየም የተለያዩ ተሽከርካሪዎችንና ማሽነሪዎችን የሚያስመጡ፣ የሚገጣጥሙ እና የሚያመርቱ ድርጅቶች ምርቶቻቸውን አስተዋውቀዋል።
//****
ህዳር 20/2017
አዲስ አበባ