ዋስትና ሕንጻ - ጅማ

ዋስትና ሕንጻ - ጅማ

በታሪካዊው የአባ ጅፋር ቤተ-መንግሥት፣ በቡና መገኛነቷና በለምለም ተፈጥሮዋ የምትታወቅ የንግድና የባሕል ማዕከል ስትሆን፤ የጥንታዊ ታሪክና የዘመናዊ ዕድገት መገኛ የሆነች የምዕራብ ኢትዮጵያ ዕንቁ ከተማ ናት - ጅማ ።

በተፈጥሮ ሀብቷ በምትታወቀው ጅማ ከተማ የተገነባው የዋስትና ሕንጻ ግንባታው አልቆ ለምርቃት ዝግጁ ሆኗል።

ሕንጻው በውስጡ የደቡብ ምዕራብ ሪጅን ጽ/ቤትን ይዟል። ለቢሮ አገልግሎት፣ ለካፌና ሬስቶራንት፣ ለህክምና መስጫ ማዕከላት፣ ለተለያዩ መዝናኛዎችና ለሌሎችም የንግድ አገልግሎቶች እንዲውልና ለከተማዋ ተጨማሪ ውበት እንዲሆን የተሰራ ዘመናዊ ሕንጻ ነው፡፡

ስለሕንጻው አንዳንድ መረጃዎች

👉 የህንጻው ግንባታ በ2017 የተጀመረ ሲሆን፣ በ2018 ተጠናቋል።
👉 ህንጻው የሚገኝበት ቦታ -- ጅማ ከተማ አባጅፋር ማዞሪያ
👉 የህንጻው ከፍታ +38.80 ሜትር ሲሆን፣ ባለ 8 ወለል ነው።
👉 ሀይል ቆጣቢ 1 ዘመናዊ ሊፍት ተገጥሞለታል
👉 መብራት በሌለበት ጊዜ በራሱ የሚነሳ (Automatic) ዘመናዊ ጀኔሬተር እና UPS ያለው
👉 በአንድ ጊዜ 20 ያህል ተሸከርካሪዎችን ማስተናገድ የሚችል 1 ቤዝሜንት እና ዘመናዊ የፓርኪንግ አስተዳደር ስርዓት ያለው፣
👉 በፓርኪንግ ውስጥ የሚፈጠርን ከፍተኛ ሙቀት ለመቀነስ የፓርኪንግ አየር ማናፈሻ /Car parking ventilation/ የተሟላለት
👉 ዘመናዊ የሴኩሪቲ ካሜራ (CCTV)፣ ዲጂታል ቪዲዮ ቀረጻ (DVR/NVR) ስርዓት የተገጠመለት
👉 የድንገተኛ አደጋ ጊዜ ማሳወቂያ አላርም/ድምጽ ማሰማት የሚችል፣
👉 ተንቀሳቃሽ የእሳት ማጥፊያዎች፣ የእሳት ማጥፊያ ቱቦዎች፣ የሃይድሪቲ ሲስተም ተገጥሞለታል።
            የመንግሰት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር

Share this Post