ዋስትና ሕንጻ - ሀዋሳ
ዋስትና ሕንጻ - ሀዋሳ
የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር በቅርቡ ከሚያስመርቃቸው 8 ሕንጻዎች መካከል አምስቱን አስተዋውቀናችኋል።
ለዛሬ ደግሞ በሃዋሳ ከተማ ስለሚገኘው ሌላኛው የአስተዳደሩ ሕንጻ መረጃዎችን እናጋራለን።
ሕንጻው ባሕርዳር ከሚገኘው የዋስትና ህንጻ ጋር ተመሳሳይ ዲዛይን ያለው ሲሆን፣ ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል። የደቡብ ሪጅን ጽ/ቤትን በውስጡ የያዘው ህንጻው፣ ለቢሮ አገልግሎት፣ ለካፌና ሬስቶራንት፣ ለህክምና መስጫ ማዕከላት፣ ለተለያዩ መዝናኛዎችና ለሌሎችም የንግድ አገልግሎቶች እንዲውል ተደርጎ የተሰራ ነው፡፡
ስለሕንጻው አንዳንድ መረጃዎች
👉 የህንጻው ግንባታ በ2015 የተጀመረ ሲሆን፣ በ2017 ተጠናቋል።
👉 ህንጻው የሚገኝበት ቦታ -- ሀዋሳ ከተማ ቤተሰብ መምሪያ ጎን
👉 የህንጻው ከፍታ +40.25 ሜትር ሲሆን፣ ባለ 8 ወለል ነው።
👉 ሀይል ቆጣቢ 5 ዘመናዊ ሊፍቶች የተገጠሙለት
👉 መብራት በሌለበት ጊዜ በራሱ የሚነሳ (Automatic) ዘመናዊ ጀኔሬተር እና UPS ያለው
👉 በአንድ ጊዜ 20 ያህል ተሸከርካሪዎችን ማስተናገድ የሚችል 1 ቤዝሜንት እና ዘመናዊ የፓርኪንግ አስተዳደር ስርዓት ያለው፣
👉 ዘመናዊ የሴኩሪቲ ካሜራ(CCTV)፣ ዲጂታል ቪዲዮ ቀረጻ (DVR/NVR) ስርዓት የተገጠመለት
👉 የድንገተኛ አደጋ ጊዜ ማሳወቂያ አላርም/ድምጽ ማሰማት የሚችል፣
👉 ተንቀሳቃሽ የእሳት ማጥፊያዎች፣ የእሳት ማጥፊያ ቱቦዎች፣ የሃይድሪቲ ሲስተም ተገጥሞለታል።
የመንግሰት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር