የዓለም የኤድስ ቀን፣ የፀረ-ጾታ ጥቃት እና የፀረ-ሙስና ቀኖች ተከበሩ
የዓለም የኤድስ ቀን፣ የፀረ-ጾታ ጥቃት እና የፀረ-ሙስና ቀኖች ተከበሩ
የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር አመራሮችና ሠራተኞች የዓለም የኤድስ ቀን፣ የፀረ-ጾታ ጥቃት እና የፀረ-ሙስና ቀኖችን ህዳር 26 ቀን 2018 በዋናው መ/ቤት አከበሩ።
በበዓሎቹ አከባበር ላይ የተገኙት የአስተዳደሩ የኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጥላሁን በቀለ እንዳሉት በዓሎች የሚከበሩበት ዓላማ በዋናነት በማህበረሰባችን ላይ የሚያስከትሉትን የማህበራዊ፣ የኢኮኖሚያዊና የፖለቲካዊ ችግሮች ላይ ግንዛቤ ለመፍጠርና አስቀድሞ ለመከላከል ነው።
ጾታዊ ጥቃት የሚያስከትለውን አሉታዊ ተጽዕኖ ከግምት ውስጥ በማስገባት በተለያዩ ሕጎችና አሠራሮች የሴቶችና ሕጻናት ሰብዓዊ መብት መከበር እንዲረጋገጥ ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ በመሆኑ በሴቶች ላይ የሚቃጡ ጥቃቶችን መከላከል የሁላችንም ድርሻ ነው ብለዋል።
ከኤች አይ ቪ/ኤድስ ጋር በተያያዘም አስተዳደሩ የቫይረሱን ስርጭት አሳሳቢነት ግንዛቤ ውስጥ በማስገባትና የዕቅዱ አካል በማድረግ እየሰራበት እንደሚገኝ የጠቀሱት ም/ዋና ስራ አስፈጻሚው በአስተዳደሩ በተቋቋመው የኤች አይ ቪ/ኤድስ ፈንድም ቫይረሱ በደማቸው ለሚገኝ 22 የተቋሙ ከፀረ-ሙሰና ቀን አከባበር ጋር በተያያዘም ለዜጎች ግልፅነት እና ተጠያቂነትን ያማከለ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እንዲያስችል ለተቋሙ አመራሮች፣ በየደረጃው ላሉ የስራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ግንዛቤ የመፍጠር፣ አስቸኳይ የሙስና መከላከል ጥናት የማድረግ፣ የማካሄድ እንዲሁም የሙስና ጥቆማዎችን በመቀበል የመከታተል ስራዎች ተከናውነዋል ብለዋል።
በቅርቡ የተጀመረውና ውጤታማ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኘው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትም ሙስናን እና ብልሹ አሠራርን በመከላከል ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከቱን የገለጹት ም/ዋና ስራ አስፈጻሚው በስነ-ምግባር የታነፀ ትውልድ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ሁላችንም ግንባር ቀደም ተሳታፊ ልንሆን ይገባል ብለዋል።
ለ21ኛ ጊዜ”ትውልድን በሥነ-ምግባር፣ ተቋምን በአሠራር!” በሚል መሪ ሃሳብ በተከበረው የጸረ ሙስና ቀን ላይ የአስተዳደሩ ሠራተኞች ሙስናን ለመከላከል ያላቸውን ዝግጁነት ለመግለጽ ባለ 5 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል።
ለግማሽ ቀን በተከናወነው የበዓላቱ አከባበር ላይ የአስተዳደሩ አመራሮች፣ የስራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች እንዲሁም የመሀል ሪጅን ፅ/ቤት ሠራተኞች ተገኝተዋል።