የፀረ-ኤች አይ ቪ/ኤድስ ቀን ተከበረ

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳባ ኦሪያ በበዓሉ ዕለት እንዳሉት በኤች አይ ቪ/ኤድስ እየተጠቁ ያሉት በአብዛኛው ወጣትና አምራች ዜጎች መሆናቸውን እንዲሁም የቫይረሱ ስርጭትም እየቀነሰ አለመሆኑን እና ከፍተኛ መዘናጋትም ዋጋ እያስከፈለን ነው፡፡ ኤጀንሲውም የኤች አይ ቪ/ኤድስ ጉዳይን በዕቅዱ በማካተትና በዘርፉም የአመራሩንና ፈጻሚውን ግንዛቤ ለማሳደግ የተለያዩ መድረኮች እንዲዘጋጁ አድርጓል ብለዋል፡፡ ከሠራተኞች በሚሰባሰብ መዋጮም የኤች አይ ቪ/ኤድስ ፈንድ በማቋቋም ቫይረሱ በደማቸው ለሚገኝ ሠራተኞች በየወሩ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም ‹‹ሠላም ይስፈን፤ በሴቶችና ሕጻናት ላይ የሚደርስ ጥቃት ይቁም!›› በሚል መሪ ሃሳብ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ30ኛ ጊዜ የተከበረው የፀረ-ጾታ ጥቃት ቀን ሴቶችንና ህጻናትን ከጥቃት መጠበቅ ሀገራዊ ግዴታ ብቻ ሳይሆን ሰብአዊ መብትን ማረጋገጥም ጭምር በመሆኑ፣ ጾታን መሠረት ያደረገ ጥቃትን ለመከላከል በስርዓተ ጾታ ጉዳይ ላይ የሚታዩ የተዛቡ አመለካከቶችን በማስወገድ በሴቶች ላይ የሚቃጡ ጥቃቶችን መከላከል የሁላችንም ኃላፊነት ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡

በዕለቱም በኤች አይ ቪ/ኤድስ እና በሾተላይ ምንነትና መከላከያ መንገዶች ላይ ግንዛቤ የሚያስጨብጡ ውይይቶች ተካሂደዋል፡፡

 

Share this Post