በሁለተኛው የብልፅግና መደበኛ ጉባዔ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ተካሄደ

በሁለተኛው የብልፅግና መደበኛ ጉባዔ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ተካሄደ

==============//==========

የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ሰራተኞች የብልፅግና ፓርቲ በሁለተኛው መደበኛ ጉባዔ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ የካቲት 13/2017 ዓ.ም የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ውይይት አካሄዱ፡፡

 

በውይይት መድረኩ ሰፋ ያለ ማብራሪ የተሰጠ ሲሆን በተለይ የጠንካራ ፓርቲ ግንባታን አጠናክሮ ከማስቀጠል፣ ብሔራዊነት ገዥ ትርክት ግንባታ ከማጠናከር፣ ውጤታማ የሰላም ግንባታ ሥራ ከመስራት፣ የፍትህ ዘርፍ ውጤታማነትን ከማሳደግ፣ የሀገር ግንባታ/ Nation building/ ከማጠናከር፣ የኢኮኖሚ ልማትን ከማፋጠን፣ ማህበራዊ ብልጽግናን የሚያረጋግጡ ሥራዎችን በውጤታማነት ከማስቀጠል፣ ውጤታማ የዲፕሎማሲ ሥራዎችን ከመስራት፣ የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ውጤታማነትን ከማረጋገጥ እና ጠንካራ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሥራ ከመስራት አንጻር በትኩረት መስራት እንደሚገባ በዝርዝር ቀርቧል፡፡

 

ተሳታፊዎችም በቀረበው ሰነድ ላይ ሰፋ ያለ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ያነሱ ሲሆን የጉባኤውን ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች ህዝብን በሚጠቅም መልኩ እንዲተገበሩ ጥልቅ ግንዛቤና የጋራ ርብርብ በማድረግ የመንግስት ሰራተኛው የበኩላችሁን ሚና መወጣት እንደሚገባቸው ተመላክቷል።

 

ሁለተኛው የብልፅግና ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ ከጥር 23 - 25 ቀን 2017 በአዲስ አበባ ከተማ በዐድዋ ድል መታሰቢያ አዳራሽ መካሄዱ ይታወሳል።

 

//****

የካቲት 13/2017 ዓ.ም

አዲስ አበባ

Share this Post