አስተዳደሩ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄደ

አስተዳደሩ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄደ

 

 

የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ጨፌ ኮንዶሚኒየም በሚባለው አካባቢ ሰኔ 23/2015 የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄዱ።

አስተዳደሩ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተሳካ እንዲሆን በየዓመቱ በተለያዩ አካባቢዎች ችግኝ የመትከል እና የመንከባከብ ስራዎችን የሚያከናውን ሲሆን፣ በዕለቱም ‘ነገን ዛሬ እንትከል’ በሚል መሪ ሃሳብ 1500 የተለያዩ የችግኝ ዓይነቶችን በመትከል በአረንጓዴ ልማት ላይ የሚያደርገውን ተሳትፎ ቀጥሎበታል።

በዕለቱ ጨፌ ኮንዶሚኒየም ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በተካሄደው የችግኝ ተከላ ስነስርዓት ላይ የዋናው መስሪያ ቤት እና የመሃል ሪጅን ጽ/ቤት የስራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።

Share this Post