የአስተዳደሩ አመራሮች እና ሰራተኞች በአንድ ጀንበር 600 ሚሊየን ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ላይ በመሳተፍ አረንጓዴ አሻራቸውን አሳረፉ

የአስተዳደሩ አመራሮች እና ሰራተኞች በአንድ ጀንበር 600 ሚሊየን ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ላይ በመሳተፍ አረንጓዴ አሻራቸውን አሳረፉ
===========//============
የአስተዳደሩ አመራሮች እና ሠራተኞች በአንድ ጀንበር የተያዘዉን 600 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ስኬት አስተዋፅኦ ለማድረግ በጫካ ፕሮጀክት እና በየካ ተራራ (ጅፋራ በር) አከባቢ በመገኘት የደን ሽፋንን የሚያሳድጉ፣ ለአካባቢ ጥበቃ አስተዋጽኦ የሚያደርጉና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ተከሉ።

በችግኝ ተከላዉ ላይ ከአስተዳደሩ ዋና መ/ቤት፤ ከመሀል ሪጅን እና ከአዲስ አበባ ሪጅን በአጠቃላይ ከ 150 በላይ አመራሮች እና ሠራተኞች የተሳተፉ ሲሆን የተተከለዉን ችግኞች ማህበረሰብ በማንከባከብ ተጠቃሚ እንዲሆን ተሳታፊዎች ገልጻል።

//**

ነሐሴ 17/ 2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ

Share this Post