አስተዳደሩ በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች የግንዛቤ ማስጨበጫና የግምግማ መድረክ አካሄደ፡፡
የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ፈንድ አስተዳድር ሚያዝያ 21/2014 ዓ.ም በአስተዳደሩ የመሰብሰብያ አዳራሽ በአዲሱ የተሻሻለዉ አዋጅ ቁጥር 1267/2014 እና የ9 ወር እቅድ አፈፃፀም እንዲሁም በወቅታዊ የቀጣይ 3 ወራት እቅድ ዙሪያ ለዋና መ/ቤት ሰራተኞች የግንዛቤ ማሰጨበጫ መድረክ እና ግምገማ አካሂድዋል፡፡
የግንዛቤ ማሰጨበጫ መድረኩ የተገኙት የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ፈንድ አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳባ ኦርያ በመከፈቻ ንግግራቸዉ ፤አዋጁን ለማስፀደቅ ፈታኝ የነበሩ ጉዳዮችን ሲገልፁ የም/ቤት አባላት አዲስ በመሆናቸው እንደ አዲስ ስለ አዋጁና ስለተቋሙ ማስገንዘብ አስፈላጊ ስለነበረ ማስገንዘብ እስኪቻል ድረስ አዋጁ የዘገየ መሆኑን ተናግሯል፡፡
በተጨማሪም ዋና ዳይሬክተሩ የቀጣይ 3 ወራት ወቅታዊ እቅዶችንም ከመደበኛ ስራችን ጋር የተያያዙ ስለሆኑ ጎን ለጎን በመተባበርና በመደጋገፍ መስራት እንደሚያስፈልግ ለተሳታፊዎች ገልጸዋል፡፡
የተሻሻለዉ አዋጅ ፅሁፍ አቅራቢዉ ባለሙያዉ በበኩላቸዉ ፡- አዋጁን ማሻሻል ያስፈለገበት ዋና አላማ ተቋሙ የጡረታ ፈንዱን ቀጣይነት ለማረጋገጥ እና ለማዳበር በተጠኑ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ መሰማራት፣ከዚህ በፊት የተጠቀምንባችውን አዋጆች በማሻሻል ወጥ ለማድረግ እና ስርዓቱ ተጠናክሮ መቀጠል ለማህበራዊ ፍትህ፣ ለምርታማነትና ለልማት ጉልህ አስተዋፅኦ ስለሚኖረው መሆኑን ተናግሯል፡፡ በቀረበዉ የተሻሻሉ የአዋጁ ጉዳዮች ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄና አስተያየቶች በሙሉ ዝርዝር ማብራሪያ ለሚያስፈልጋቸው ሰፊ ገለፃ ተሰጥቶባችዋል፡፡
በተመሳሳይም በመድረኩ የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በዚሁ መድረክ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በቀጣይ 3 ወራት የሚከናውኑ ወቅታዊ ስራዎች እቅድ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን አፈጻጸም ማሳደግ፣ የስራ እደልን መፍጠር፣ የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ የተለያዩ ስራዎችን መስራት ይቻል ዘንድ ለዚህም የሚከታተል ኮሚቴ እንዲቋቋም በማድረግና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መቶ በመቶ እንዲፈቱ ማስቻል እና በእስታንዳርዱ መሰረት አገልግሎት መስጠት ከተያዙት እቅዶች ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡