ዋስትና የንግድ ማዕከል

ዋስትና የንግድ ማዕከል 
=====//=======
የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር በቅርቡ ከሚያስመርቃቸው 8 ሕንጻዎች መካከል የዋና መ/ቤት፣ ፒያሳ ሊሴ ገ/ማሪያም ት/ቤት ጀርባ እና ቦሌ ኦሎምፒያ አካባቢ ስለሚገኘው ሕንጻዎች የተመለከቱ መረጃዎችን አካፍለናችኋል።

ለዛሬ ደግሞ ስለ ዋናው እና ግዙፉ የዋስትና ንግድ ማዕከል አንዳንድ መረጃዎችን እናጋራለን።

ዋስትና የንግድ ማዕከል አስተዳደሩ የጡረታ ፈንዱን አስተማማኝነት ለማረጋገጥ በማቋቋሚያ ደንቡ በአዋጭና አትራፊ የኢንቨስትመንት መስኮች ላይ እንዲሰማራ ሲፈቀድለትና ወደ ሪፎርም ከገባ በኋላ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገነባ አስደማሚ እና ማራኪ ሕንጻ ነው። 

ሕንጻው ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ በርካታ የንግድ እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በኪራይ እየተገለገሉበት ይገኛል፡፡

ስለሕንጻው አንዳንድ መረጃዎች

👉 የህንጻው ግንባታ የተጀመረው በ2010 ነው።
👉 ህንጻው የሚገኝበት ቦታ -- ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል ጀርባ።
👉 የህንጻው ከፍታ + 82.40m ሜትር ሲሆን፣ ባለ 19 ወለል ሕንጻ ነው።
👉 በአንድ ጊዜ 200 ያህል ተሸከርካሪዎችን ማስተናገድ የሚችል 4 ቤዝሜንት እና ዘመናዊ የፓርኪንግ አስተዳደር ስርዓት አለው፣
👉 ሀይል ቆጣቢ 8 ዘመናዊ ሊፍት እና እስከ 5ኛ ወለል ድረስ ደግሞ 6 ተንቀሳቃሽ ደረጃ /escalators/ የተገጠመለት ነው።
👉 የከርሰ ምድር ውሃ አለው።
👉 ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች የተገጠሙለት የተለያዩ የስብሰባ አዳራሾች እና ሲኒማ ቤት አለው።
👉 መብራት በሌለበት ጊዜ በራሳቸው የሚነሱ (Automatic) ሁለት ዘመናዊ ጀኔሬተር እና UPS የተገጠመለት ነው።
👉 ዘመናዊ የሴኩሪቲ ካሜራ (CCTV) የተገጠመለት ነው።
👉 የድንገተኛ አደጋ ጊዜ ማሳወቂያ አላርም/ድምጽ ማሰማት የሚችል።
👉 ተንቀሳቃሽ የእሳት ማጥፊያዎች፣ የእሳት ማጥፊያ ቱቦዎች፣ የሃይድሪቲ ሲስተም የተገጠመለት ነው።
               
ለዋስትናዎ እንተጋለን !

የመንግሰት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር
                                       አዲስ አበባ

Share this Post