የዋስትና ሕንጻዎች
የዋስትና ሕንጻዎች
=====//=====
የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር በቅርቡ ከሚያስመርቃቸው 8 ሕንጻዎች መካከል በአዲስ አበባ ፒያሳ ከዋስትና የንግድ ማዕከል ጀርባ ያስገነባው የዋና መ/ቤት እና ፒያሳ ሊሴ ገ/ማሪያም ት/ቤት ጀርባ ስለሚገኘው ዋስትና ሕንጻዎች የተመለከቱ አንዳንድ መረጃዎችን አካፍለናችኋል።
ለዛሬ ደግሞ ቦሌ ኦሎምፒያ አካባቢ ስለሚገኘው ሦስተኛው የአስተዳደሩ የዋስትና ሕንጻ መረጃዎችን እናጋራለን።
የሕንጻው ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ለቢሮ አገልግሎት፣ ለካፌና ሬስቶራንት፣ ለህክምና መስጫ ማዕከላት፣ ለተለያዩ መዝናኛዎች የሚሆን ቴራስና ለሌሎችም የንግድ አገልግሎቶች እንዲውል ተደርጎ የተሰራ ነው፡፡
ስለሕንጻው አንዳንድ መረጃዎች
👉 የህንጻው የሚገኝበት ቦታ -- ቦሌ ኦሎምፒያ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ።
👉 የህንጻው ከፍታ +65.60m ሜትር ሲሆን፣ ባለ 17 ወለል እና ለዕይታ ምቹ የሆነ ቴራስ አለው፣
👉 ሀይል ቆጣቢ 2 ዘመናዊ ሊፍት የተገጠመለት ነው፣
👉 የከርሰ ምድር ውሃ ያለው ነው፣
👉 መብራት በሌለበት ጊዜ በራሱ የሚነሳ (Automatic) ዘመናዊ ጀኔሬተር እና UPS የተገጠመለት።
👉 በአንድ ጊዜ 30 ያህል ተሸከርካሪዎችን ማስተናገድ የሚችል 2 ቤዝሜንት እና ዘመናዊ የፓርኪንግ አስተዳደር ስርዓት ያለው፣
👉 ዘመናዊ የሴኩሪቲ ካሜራ (CCTV) የተገጠመለት ነው፣
👉 የድንገተኛ አደጋ ጊዜ ማሳወቂያ አላርም/ድምጽ ማሰማት የሚችል፣
👉 ተንቀሳቃሽ የእሳት ማጥፊያዎች፣ የእሳት ማጥፊያ ቱቦዎች፣ የሃይድሪቲ ሲስተም የተገጠመለት ነው።
👉 ሕንጻው የሚገኝበት አካባቢ ለዕይታ ማራኪ ሲሆን፣ ለማንኛውም ዓይነት የንግድም ሆነ አገልግሎት መስጫ ተመራጭ ነው። በመሆኑም ጥቂት ቦታዎች የቀሩ በመሆኑ መከራየት የሚፈልግ ካለ ሳያልቅ አሁኑኑ መከራየት ይችላል።
የመንግሰት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር
አዲስ አበባ