የዋስትና ህንጻዎች
የዋስትና ህንጻዎች
=======/======
የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር በቅርቡ ከሚያስመርቃቸው 8 ሕንጻዎች መካከል አዲሱን የዋና መ/ቤት ሕንጻ የተመለከቱ አንዳንድ መረጃዎችን ማጋራታችን ይታወሳል።
ለዛሬ ደግሞ ፒያሳ ሊሴ ገ/ማሪያም ት/ቤት ጀርባ ስለሚገኘው አስደማሚው የአስተዳደሩ ሕንጻ መረጃዎችን እናካፍላችሁ። የሕንጻው ግንባታ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ የሆነ ሲሆን ለቢሮ አገልግሎት፣ ለካፌና ሬስቶራንት፣ ለህክምና መስጫ ማዕከላት፣ ለተለያዩ መዝናኛዎች የሚሆን ቴራስና ለሌሎችም የንግድ አገልግሎቶች እንዲውል ተደርገው የተሰራ ነው፡፡
ስለሕንጻው አንዳንድ መረጃዎች
👉 የህንጻው ግንባታ የተጀመረው በ 2016 ዓ.ም ነው፣
👉 የህንጻው ከፍታ 65 ሜትር ሲሆን 14 ወለል እና ቴራስ አለው፣
👉 ሀይል ቆጣቢ 4 ዘመናዊ ሊፍት የተገጠመለት ነው፣
👉 መብራት በሌለበት ጊዜ በራሱ የሚነሳ (Automatic) ዘመናዊ ጀኔሬተር እና UPS የተገጠመለት ነው፣
👉 በአንድ ጊዜ ከ40 በላይ ተሸከርካሪዎችን ማስተናገድ የሚችል 3 ቤዝሜንት እና ዘመናዊ የፓርኪንግ አስተዳደር ስርዓት አለው፣
👉 ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች የተገጠሙለት የተለያየ መጠን ያላቸው የስብሰባ አዳራሾች አሉት፣
👉 ዘመናዊ የሕንጻ አስተዳደር ስርዓት አለው፣
👉 የሴኩሪቲ ካሜራ (CCTV) ዲጂታል ቪዲዮ ቀረጻ (DVR/NVR) ስርዓት የተገጠመለት ነው፣
👉 የአየር ማቀዥቀዣ (AC) ሲስተም የተገጠመለት እና የድንገተኛ አደጋ ጊዜ ማሳወቂያ አላርም/ድምጽ ማሰማት የሚችል፣
👉 ተንቀሳቃሽ የእሳት ማጥፊያዎች፣ የእሳት ማጥፊያ ቱቦዎች፣ የሃይድሪቲ ሲስተም የተገጠመለት ነው፣
👉 በአጠቃላይ ለየትኛውም ንግድ ምቹ የሆነ ቦታ እና አሰራረር የተሰራ ነው፡፡
👉 ለአገልግሎት መከራየት የሚፈልግ ካለ ሳያልቅ አሁኑኑ መከራየት ይችላል፡፡
የመንግሰት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር
አዲስ አበባ