አዲሱ የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ዋና መ/ቤት ህንጻ

አዲሱ የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ዋና መ/ቤት ህንጻ
        ========//=========
የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር እንደ አገር የተጀመረውን ሪፎርም ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በርካታ ለውጦችን አስመዝግቧል። ከነዚህም ለውጦች መካከል በዋናነት የሚጠቀሱትና በቅርቡ ለምረቃ የሚበቁት 8 ሕንጻዎች ተጠቃሾች ናቸው።

የእነዚህ 8 ህንጻዎች ግንባታ ዋና ዓላማ የማህበራዊ ዋስትና ፈንድ አስተማማኝነትን ለማረጋገጥ፣ በሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ እና በከተሞቻችን የተጀመረውን በጎ ገጽታ ለመገንባት የራሱን አስተዋጸኦ ለማበርከት ነው። 

አስተዳደሩ በአዲስ አበባ ፒያሳ ከዋስትና የንግድ ማዕከል ጀርባ ያስገነባው የዋና መ/ቤት ሕንጻ ግንባታው ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆኗል።

ስለሕንጻው አንዳንድ መረጃዎች

👉 የህንጻው ግንባታ የተጀመረው በ 2016 ዓ.ም ነው፣
👉 የህንጻው ከፍታ 80 ሜትር ሲሆን 17 ወለል አለው፣
👉 ሀይል ቆጣቢ 3 ዘመናዊ ሊፍት የተገጠመለት ነው፣
👉 መብራት በሌለበት ጊዜ በራሱ የሚነሳ (Automatic) ዘመናዊ 2 ጀኔሬተር፣ 2 ትራንስፎርመር እና UPS የተገጠመለት።
👉 በአንድ ጊዜ ከ30 በላይ ተሸከርካሪዎችን ማስተናገድ የሚችል 3 ቤዝሜንት እና ዘመናዊ የፓርኪንግ አስተዳደር ስርዓት ያለው፣
👉 የቢሮ በሮች Door Access Control System የተገጠመላቸው ሲሆን የሚከፈቱት በካርድ፣ በፒን ኮድ፣ በጣት አሻራ ወይም በስማርት ሰልክ የሚከፈቱ ናቸው፣
👉 የቢሮ መብራቶች ኃይል ቆጣቢ እና በሴንሰር የሚሰሩ ናቸው፣
👉 ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች የተገጠሙለት የስብሰባ አዳራሾች አሉት፣
👉 የሕጻናት ማቆያ ማዕከል፣ የጂም አገልግሎት መስጫ ክፍሎች እንዲሁም ዘመናዊ ኪችኖች አሉት፣
👉 ዘመናዊ የሕንጻ አስተዳደር ስርዓት ያለው እና የሴኩሪቲ ካሜራ (CCTV) የተገጠመለት ነው፣
👉 የአየር ማቀዥቀዣ (AC) ሲስተም የተገጠመለት እና የአደጋ ጊዜ አላርም/ድምጽ ማሰማት የሚችል፣
👉 ዘመናዊ የእሳት አደጋ መከላከያ የተገጠመለት እና በአጠቃላይ በዘመኑ የስነ-ጥበብ ህንጻ ሥራ መሠረት የተሰራ ህንጻ ነው። 

የመንግሰት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር
አዲስ አበባ

Share this Post