አስተዳደሩ የአንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት አካሄደ

አስተዳደሩ የአንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት አካሄደ

=========//===========

የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የ2017 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት አካሄደዋል።

 

በዚህ የውይይት መድረክ አስተዳደሩ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ያከናወናቸዉን ስራዎች ለውይይት የቀረበ ሲሆን በሪፖርቱ ከተጠቀሱት ውስጥ በዋናነት የምዝገባና አበል ውሳኔ አገልግሎት፣ የመረጃ ተደራሽነትን በቴክኖሎጂ የማሻሻል፣ የጡረታ ፈንድ ገቢን የማሳደግ፣ የአሠራር ስርዓትን የማሻሻል፣ የክትትልና የቁጥጥር ስራዎችን የማጠናከር፣ የሰው ሃይል ልማትና ክህሎት ማሳደግ፣ የስራ አካባቢ ምቹነትና የማህበራዊ ድጋፍ ስራዎችን የማሳደግ ተግባራት ተከናውነዋል የተባለ ሲሆን፣ በሩብ ዓመቱም የዕቅዱን 91 በመቶ መፈጸሙም ተገልጿል።

 

ከዕቅድ አፈጻጸም ዉይይት በተጨማሪ ለተሳታፊዎች በመልካም አስተዳደርና በአገልግሎት አሰጣጥ፤ በስራ አፈጻጸም እና በውጤት ተኮር ምዘና መመሪያ፣ በኦዲት ግኝት፣ በሱፐርቪዥን ግብረመልስ፣ በመልካም አስተዳደር ዕቅድ፣ በዜጎች ቻርተር ረቂቅ ሠነድ እና በመንግስት የመቶ ቀን አፈጻጸም ላይ ውይይት ተካሂዷል።

 

በውይይት መድረኩ ላይ እንደተገለጸው በቀጣይ ዝቅ ያለ አፈጻጸም የተመዘገበባቸውን ተግባሮች ከዋና መስሪያ ቤት እስከ መስክ ጽ/ቤት ድረስ በጋራ እና በተናበበ አካሄድ ስራዎችን ማከናወን እንደሚገባ አቅጣጫ ተቀሚጠዋል።

 

ከጥቅምት 19-22/2017 ድረስ ለተከታታይ አራት ቀናት በቢሾፍቱ ከተማ በተካሄደው የዚህ የዕቅድ አፈጻጸምና የስልጠና መድረክ ላይ የተቋሙን አመራሮች ጨምሮ የሪጅን ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና የዋናው መ/ቤት የስራ ኃላፊዎች ተካፍለዋል።

 

//****

ጥቅምት 22/2017

ቢሾፍቱ

Share this Post