ለአስተዳደሩ ሠራተኞች ስልጠና ተሰጠ
ለአስተዳደሩ ሠራተኞች ስልጠና ተሰጠ
የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር በዋናው መስሪያ ቤት፣ በሪጅን እና በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ለሚገኙ ሁሉም ሠራተኞች ከታህሳስ 22 እስከ 25 ድረስ በቪዲዮ ኮንፈረንስ ስልጠና ሰጠ።
በሁለት ዙር በተሰጠው በዚህ ስልጠና የተቋሙን አገልግሎት አሠጣጥ ያሻሽላሉ የተባሉ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች የተነሱ ሲሆን፣ በዋናነትም በጡረታ አዋጅ 1267/2014 ማስፈጸሚያ መመሪያ 959/2015፣ በጡረታ መዋጮ ገቢ አሠባሰብ መመሪያ፣ በስራ ላይ ስነ ምግባር፣ በለውጥ ሥራ አመራርና አገር በቀል ኢኮኖሚ ሪፎርም፣ በተቋሙ ሪፎርምና ትግበራ እንዲሁም በተቋማዊ ተግባቦት ላይ ትኩረት አድርገዋል።
በስልጠናው ላይ እንደተገለፀው በቀጣይም በአሠራር ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን በመለየት ተከታታይ ስልጠና ይሰጣል የተባለ ሲሆን፣ ሠራተኞችም የተቋሙን ሪፎርም በማስቀጠል እና በአገልግሎት አሠጣጥ ላይ አዎንታዊ ለውጥ በማምጣት ጠንክረው ሊሰሩ ይገባል ተብሏል።
በቪዲዮ ኮንፈረንስ በሁለት ዙር በተሰጠው በዚህ ስልጠና ሁሉም የአስተዳደሩ ሠራተኞች የተሳተፉ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል።