ዋስትና ህንጻ - በውብቷ ባሕር ዳር ከተማ
ዋስትና ህንጻ - በውብቷ ባሕር ዳር ከተማ
የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር በቅርቡ ከሚያስመርቃቸው 8 ግዙፍ ሕንጻዎች መካከል አንዱ የሆነውና በውብቷ ባሕር ዳር ከተማ የሚገኘው ሕንጻ ግንባታው ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆኗል።
ይህ ባለ 8 ወለል ዘመናዊ ሕንጻ የሰሜን ምዕራብ ሪጅን ጽ/ቤትን በውስጡ የያዘ ሲሆን፣ ለተለያዩ የንግድ ዘርፎች ምቹ ተደርጎ ተገንብቷል።
ሕንጻው ምን ምን ያካትታል?
✅ ለቢሮ፣ ለካፌና ሬስቶራንት፣ ለሕክምና ማዕከላትና ለመዝናኛዎች የሚሆኑ ሰፊ ቦታዎች።
✅ 5 ዘመናዊና ኃይል ቆጣቢ ሊፍቶች።
✅ መብራት ሲቋረጥ በራሱ የሚነሳ ጀነሬተር (Automatic) እና UPS።
✅ 20 ተሸከርካሪዎችን የሚያስተናግድ ቤዝሜንት ፓርኪንግ።
✅ አስተማማኝ የሴኩሪቲ ካሜራ (CCTV) እና ዲጂታል ቀረጻ ስርዓት።
✅ ዘመናዊ የድንገተኛ አደጋ መከላከያና የእሳት አደጋ ማጥፊያ ስርዓት።
📍 ቦታ፡ ባሕር ዳር ከተማ፣ ቀበሌ 13 (የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ጀርባ)።
📏 ከፍታ፡ 40.25 ሜትር (ባለ 8 ወለል)።
ለዋስትናዎ እንተጋለን
የምንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር
#የመንግስትሠራተኞችማህበራዊዋስትና #ኢትዮጵያ #BahirDar