ዓለም ዓቀፉ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ እና የፀረ-ፆታ ጥቃት ቀን ተከበረ
ዓለም ዓቀፉ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ እና የፀረ-ፆታ ጥቃት ቀን ተከበረ
የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር አመራሮችና ሠራተኞች በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበሩትን የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ እና የጸረ-ፆታዊ ጥቃት ቀን በዓላትን ህዳር 27/2016 በዋናው መስሪያ ቤት አከበሩ።
በበዓላቱ አከባበር ላይ የተገኙት በአስተዳደሩ የሪሶርስ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ምስጋናው አድማሱ እንዳሉት የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ስርጭት አድማሱን እያሰፋና አዲስ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥርም እየጨመረ መሆኑን በቅርብ ጊዜ የወጡ መረጃዎች የሚያመለክቱ ሲሆን፣ ለዚህም ቀደም ሲል ይካሄዱ የነበሩ የንቅናቄ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች መቀዛቀዛቸው ለበሽታው ማገርሸት የራሱን አስተዋጽኦ አበርክቷል ያሉ ሲሆን፣ እንደተቋም በሽታውን በመከላከል ረገድ ሁላችንም ቆም ብለን ልናስብና ምርመራ ልናደርግ ይገባል ብለዋል። አክለውም በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለመከላከል ሁላችንም ከራሳችን እና ከቤታችን ጀምረን ለሴቶች የሰጠነውን ትኩረት ማየት ይገባል ብለዋል።
በበዓሉ አከባበር ላይ በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ፣ በማህጸን በር ጫፍ ካንሰር እና በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን አስመልክቶ ገለጻ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።
ዘንድሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ32ኛ ጊዜ “ፆታዊ ጥቃትን እንከላከላለን፤ መቼም፣ የትም፣ በምንም ሁኔታ ጾታዊ ጥቃትን ዝም አንበል” እንዲሁም ለ36ኛ ጊዜ “የማህበረሰብ መሪነት ለላቀ ኤች.አይ.ቪ መከላከል” በሚሉ መሪ ሃሳቦች በዋናው መስሪያ ቤት በተከበሩት በዓላት ላይ በተቋሙ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ምርመራ የተካሄደ ሲሆን፣ በዚህም 8 ወንድ፣ 12 ሴት በአጠቃላይ 20 ሠራተኞች ምርመራ አካሂደዋል።