የኤጀንሲው ሠራተኞች የመከላከያ ሠራዊትን ለማበረታታት በተካሄደው የጎዳና ላይ ሩጫ እና የእግር ጉዞ ላይ ተሳተፉ
የፌዴራል ተቋማት ሠራተኞች የተሳተፉበት እኔም ለሃገሬ ወታደር ነኝ ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ የትም፣ መቼም፣ በምንም በሚል መሪ ቃል መነሻውንና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ባደረገው የ5 ኪሜ የጎዳና ላይ ሩጫና የእግር ጉዞ ኤጀንሲውን በመወከል 80 የሚሆኑ ሠራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡