በአስተዳደሩ የሴቶች ፎረም የሪፖርትና እቅድ ውይይት አካሄደ

በመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር በዋና መ/ቤቱ የተቋቋመው የሴቶች ፎረም በ2014 በጀት አመት የፎረሙ እንቅስቃሴ እና የ2015 በጀት አመት እቅዱ ላይ ግንቦት 16/2014ዓ/ም በዋናው መ/ቤት አዳራሽ ውይይት ተካሂደዋል፡፡

የፎረሙ ሰብሳቢና የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ባዩሽ ሀይሌ ውይይቱን በንግግር ሲከፍቱ 166 አባላት እንዳሉት ከገለጹ በኋላ በተቋሙ ሴቶችን  በኢኮኖሚ ተጠቃሚ ለማድረግ ከሚሰሩ ስራዎች አንዱ መሆኑን አክለዋል፡፡

በዕለቱም በ2014 ከተደረጉት የፎረሙ እንቅስቃሴዎች መካከል ከአባላት መዋጮ መሰብሰብ፤ አዳዲስ አባላትን ማፍራት፤ እንደ አባላቱ ፍላጎት ልዩ ልዩ የቤት እቃዎችን ከተቀማጭ ገንዘብ ላይ ወጭ አድርጎ በመግዛት በ3 ወራት እንዲመልሱ በማድረግ በ3 ዙር  149 አባላት ተጠቃሚ መሆናቸውን በቀረበው   ሪፖርት ተገልጿል፡፡  በቀጣይም  እቃ ከማምጣት በተጨማሪ የአባላቱን አቅም በስልጠና የማሳደግ ፤ የአባላትን መረጃ በአግባቡ የመያዝና የአባላትን ወርሃዊ መዋጮ ከፍ የማድረግ ስራ እንደሚሰራ በመድረኩ ተብራርተዋል፡፡

ከላይ ከተገለፁት 166 አባላት ውስጥ 45ቱ ተባባሪ ወንድ አባላት መሆናቸው በመድረኩ ተገልጿል፡፡

Share this Post